Time in Ethiopia:

Showing posts with label Philosophy. Show all posts
Showing posts with label Philosophy. Show all posts

Oct 9, 2014

‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ብሎ ለጠየቀ!

ZETOBIA | Thursday, October 09, 2014

(በካሣሁን ዓለሙ)

‹ፍልስፍናን እማራለሁ› ብዬ ት/ቤት ብገባ፣ መምህሩ ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ብሎ መልሶ እኔኑ ጠየቀኝ፤ ‹ካወቅኳትም ለም
ንስ ልማራት ሒሳብ ከፈልኩ?› አልኩኝ፤ ምን ላድርግ? ቢቸግረኝ ያው ‹የፍልስፍና አስተማሪዎች ናቸው› ከሚባሉት ፋይል የሰማሁትን ስምምነታቸውን ይዤ፡- ፍልስፍና እኮ እንዲህ ነው ማለት ጀመርኩ!
በመሠረቱ ጭንቁ መልሱ ላይ ነው እንጂ የፍልስፍና አዋቂና ምጡቅ የተባለ ሁሉ ይችን ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› የምትል ጥያቄ ሳያነሳት አይቀርም፤ መምህሬም ‹ጥያቄዋ ትንሽ ገብታው ነው› መሰል የጠየቀኝ፤ እንደኔ ያላብላሉት ሳይሆኑ መልሷን ሲጭሩ የኖሩት ሊቃውንት ግን ግምታዊ መልሳቸውን ሰጥተዋል፤ እኔም በመጠኑ ሰምቻለሁ (ከፈለጋችሁ ጆሮ ጠገብ በሉኝ)፡፡ በአጠቃላይ ግን በሊቃውንቷ ‹ፍልስፍና ጥበብን ማፍቀር ናት› የሚል ስምምነት ላይ ተደርሶባታል ብሏል መምህሬ ራሱ፡፡ እንደዚህ ከሆነማ ማጠንጠኛዎቿ እነዚህ ‹ጥበብ› እና ‹ፍቀር› የሚሉ ቃላት (ጽንሣተ-ሐሣብ) ናቸው ማለት ብዬ ያዝኩ፡፡ እነዚህ ሁለት ቃላት ደግሞ ዓለምን በመሠረትነትና በዓምድነት (ምሠሦ ሆነው) ያቆሙ ኃይላት ናቸው፡፡ የፍልስፍናም ድንቅነት የተመሠረተው በእነሱ የውህድነት ጥንጣኔ ላይ ሊሆን ነው፡፡ መምህሬም ጥያቄዎቹን አከታተለ ‹እንዴት ተዋሃዱ? የውህደታቸው ጥብዓትስ እስከምን ድረስ ነው? በምን ያህል አስተውሎትስ ልንረዳቸው ቻልን? የእሴትና የኪን (የውበትን) ተውህቦስ ማን አደላቸው? ነው በራሳቸው በሌጣነት ነው አንክሮ ውስጥ የከተቱን?› የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እያነሳ አስጨነቀን! እንደተረዳሁት ከሆነ በእነሱ የተነሣ ስንቱ ሊቅ ቀውሷል፣ ስንቱም አሰላሳይ ከዘመድ ከወዳጅ ተለይቶ መንኖላቸዋል መሰላችሁ፤ ጥበብን ማፍቀር አያድርስባችሁ እቴ! (እንቢ ካላችሁም የጥበብ ስቃይን ይጣልባችሁ ብሎ መርገም ይቻላል!)
ያሳቢዎቹን ምጥቀት የፈተነውስ ጥበባዊ ፍቅሯ አይደል! ስለዚህ መምህሬም ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ሲል የፍቅርንና የጥበብን ምንነት ያውቃል ማለት ነው፤ ስለዚህ እኔ ያልገባኝ ‹ፍቅር ራሱ ምንድን ነው? ጥበብስ ለምን ልትፈቀር ቻለች?› አልኩት! እሱም በገፅታው ‹ደደብ!› እያለ በቃላት ተረከልኝ! ትንሽ አሰላስሎም ገለጻውን ‹ፍቅርን› ሊተረጉም በመሞከር ጀመረ!
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jun 30, 2014

ልቃዊነት የዘመናችን ሃይማኖት

ZETOBIA | Monday, June 30, 2014
 ካሣሁን ዓለሙ:-

ሃይማኖት በሥርዎ ቃሉ ማመንና መታመን የሚሉ ፅንሣተ-ሐሣብን የያዘ ቃል ነው፡፡ ማመን በአንድ ነገር ላይ እምነት ማሳደር ሲሆን መታመን ደግሞ ላመኑበት ነገር መታገልና መቆም ነው፡፡ ይህንን ይዘን ወደ ፍልስፍናው መከራከሪያ ስንገባ በዓለማችን የሚገኙ የሃይማኖት ይዘቶችን በሦስት ከፍለን ልንያቸው እንችላለን፡፡
1) በእግዚአብሔር ህልውነት ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት (Theist)
የእግዚአብሔር ህልውነትን በማመንና እሱን በመመሥከር እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ግኑኝነት የሚያደርግ በሥራው ፍፁም የሆነ አምላክ መሆኑን ይቀበላል፡፡ ስለሆነም የሰው ልጆች ከእነሱ በላይና ፍጹም ከኾነ ኃይል ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ፤ እሱም በመገለጥ ስለ ዐለማትና ፍጥረታት አፈጣጠር፣ ስለ ሰው ልጆች መፈጠርና ህልውና ነግሯቸዋል፤ ያነጋግራቸዋል ብሎ ያምና፤ ለዚህም ጥብቅና ቆሞ ይመሠክራል፤ ይከራከራል፡፡
2) በእግዚአብሔር አለመኖር ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት (Atheist)
ይኸ የእግዚአብሔርን ህልውነት የሚክድና ለዚያም አቋም ጥብቅና የቆመ ሃይማኖት መሰል አስተምህሮ ነው፡፡ይህም ሃይማኖት የራሱ መታወቂያ አለው፡፡ በአንድ በኩል ሰይጣንን በግል እያመለከ የእግዚአብሔርን ህልውነት የሚቃወም ሲሆን በአብዛኛው በኢሉምናቲ የሚሥጢር ማኅበራት የሚቀነቀን ነው፤ ምሥጢራዊነቱም ያመዝናል፡፡ ስለዚህ በግልፅና በተቋማዊ አደረጃጀት የማይታወቅ ቢመስልም በአብዛኛው በሳይንስና በፍልስፍና አስተምህሮ ተወሽቆ እምነቱ ተቀባይነት አግኝቶ እንዲስፋፋ ጥረት ይደረግለታል፡፡ የዚህ ሃይማኖት አቀንቃኞች በዋናነትዝግመተ ለውጠኛችና ቁሳካላዊያን ናቸው፡፡ለምሳሌ እንደ ፈርደሪክ ኒቼ፣ ካርል ማርክስ፣ ሌኒን፣ ዳሪዊን፣ ሪቻርድ ዳውኪንስና መሰሎቻቸውን መጥቀስይ ቻላል፡፡
3) ‹አሊለም› (እግዚአብሔር አለ-የለም) ሃይማኖት (Agnostic)
የእዚህ ሃይማኖት መነሻው ልቃዊነት (Liberalism) ማሳለጫው ምንፍቅና (Skeptic) ተግባሩም ውል አልባነትና ግደለሽነት (indifference) ነው፡፡ የመከራከሪያ ስልቱም ዥዋዥዌ መጫወት ነው፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jun 27, 2014

በሀልዎተ-እግዚአብሔር ዙሪያ በሻይ ቤት የተደረገ ሙግት

ZETOBIA | Friday, June 27, 2014
      (በካሣሁን ዓለሙ)


አንድ ቀን ፒያሣ በሚገኝ አንድ ኬክ ቤት ውስጥ የሃይማኖት መጽሐፍ እያነበብኩ ቁጭ ባልኩበት አንድ ዕድሜው በ20ዎቹ መጀመሪያ የሚገኝ ወጣት አጠገቤ መጥቶ በመቀመጥ ጨዋታ ጀመረ፡፡ የማነበውንም መጽሐፍ ‹እስቲ ልየው› ብሎኝ አሳየሁት፡፡ ከመጽሐፉ ጋር ተያይዞ ባነሳቸው ጥያቄዎችና ነቀፌታዎች የተነሳ የሚከተለውን ክርክር ተጨቃጭቀን ተለያየን፡፡
ልጁ ክርክሩን የጀመረውም “አሁን ይህንን መጽሐፍ ብለህ ታነባለህ?” በሚል ነበር፡፡
እኔም ተናድጄ “ለምን አላነበውም መጽሐፍ አይደለም?” ብዬ በጥያቄ መለስኩለት፡፡
“ማለቴ በዚህ መጽሐፍ ጊዜህን ከምታባክን ለምን የተሻለ እውቀት ያላቸውን መጻሕፍት አታነብም?”
“ምን ዓይነት መጻሕፍት ናቸው የተሻለ ዕውቀት ያላቸው?”
“ለምሳሌ የፍልስፍና መጻሕፍትን አታነብም? ሰዎች ለጥቅማቸው ሲሉ እግዚአብሔር ፣ ሰይጣን፣ ኃጢያት፣ ጽድቅ፣ ኩነኔ ምናምን እያሉ የጻፉትን ተረታተረት ከምትለቃቅም?” አለኝ እያጣጣለ፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Mar 17, 2014

‹‹ለእኔ የአካዳሚክ ነፃነት ችግር ሆኖ አያውቅም›› ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ

Geez Bet | Monday, March 17, 2014
ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ፣ የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትና ተገቢነት ተመራማሪ
ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ የተወለዱት አስመራ ነው፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አስመራ፣ የሁለተኛ ደረጃን ደግሞ በጅማ ነው የተከታተሉት፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአስመራ ዩኒቨርሲቲ በሕግ አግኝተዋል፡፡ ለሁለት ዓመታት ከሠሩ በኋላ ስኮላርሺፕ አግኝተው እንግሊዝ ከሄዱ በኋላ ለረዥም ዓመታት ቆይተዋል፡፡ ያጠኑት ታሪክ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትና ተገቢነትን በተለያዩ ጥናቶቻቸው ለሃያ ሦስት ዓመታት ተመልክተዋል፡፡ “Crisis of Ethiopian Education፡ Implications for nation Building, Rethinking Ethiopian Education, Ethiopian Education from Crisis to Collapse” በሚሉ ርዕሶች መጻሕፍትም አሳትመዋል፡፡ የመጀመሪያውና እ.ኤ.አ. በ1990 በሲዳ ስዊድን ድጋፍ የታተመው መጽሐፋቸው ጥሩ ተቀባይነትን
ሙሉውን አንብብ-Read More

Oct 28, 2013