Time in Ethiopia:

Showing posts with label Orthodox. Show all posts
Showing posts with label Orthodox. Show all posts

Oct 9, 2014

‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ብሎ ለጠየቀ!

ZETOBIA | Thursday, October 09, 2014

(በካሣሁን ዓለሙ)

‹ፍልስፍናን እማራለሁ› ብዬ ት/ቤት ብገባ፣ መምህሩ ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ብሎ መልሶ እኔኑ ጠየቀኝ፤ ‹ካወቅኳትም ለም
ንስ ልማራት ሒሳብ ከፈልኩ?› አልኩኝ፤ ምን ላድርግ? ቢቸግረኝ ያው ‹የፍልስፍና አስተማሪዎች ናቸው› ከሚባሉት ፋይል የሰማሁትን ስምምነታቸውን ይዤ፡- ፍልስፍና እኮ እንዲህ ነው ማለት ጀመርኩ!
በመሠረቱ ጭንቁ መልሱ ላይ ነው እንጂ የፍልስፍና አዋቂና ምጡቅ የተባለ ሁሉ ይችን ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› የምትል ጥያቄ ሳያነሳት አይቀርም፤ መምህሬም ‹ጥያቄዋ ትንሽ ገብታው ነው› መሰል የጠየቀኝ፤ እንደኔ ያላብላሉት ሳይሆኑ መልሷን ሲጭሩ የኖሩት ሊቃውንት ግን ግምታዊ መልሳቸውን ሰጥተዋል፤ እኔም በመጠኑ ሰምቻለሁ (ከፈለጋችሁ ጆሮ ጠገብ በሉኝ)፡፡ በአጠቃላይ ግን በሊቃውንቷ ‹ፍልስፍና ጥበብን ማፍቀር ናት› የሚል ስምምነት ላይ ተደርሶባታል ብሏል መምህሬ ራሱ፡፡ እንደዚህ ከሆነማ ማጠንጠኛዎቿ እነዚህ ‹ጥበብ› እና ‹ፍቀር› የሚሉ ቃላት (ጽንሣተ-ሐሣብ) ናቸው ማለት ብዬ ያዝኩ፡፡ እነዚህ ሁለት ቃላት ደግሞ ዓለምን በመሠረትነትና በዓምድነት (ምሠሦ ሆነው) ያቆሙ ኃይላት ናቸው፡፡ የፍልስፍናም ድንቅነት የተመሠረተው በእነሱ የውህድነት ጥንጣኔ ላይ ሊሆን ነው፡፡ መምህሬም ጥያቄዎቹን አከታተለ ‹እንዴት ተዋሃዱ? የውህደታቸው ጥብዓትስ እስከምን ድረስ ነው? በምን ያህል አስተውሎትስ ልንረዳቸው ቻልን? የእሴትና የኪን (የውበትን) ተውህቦስ ማን አደላቸው? ነው በራሳቸው በሌጣነት ነው አንክሮ ውስጥ የከተቱን?› የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እያነሳ አስጨነቀን! እንደተረዳሁት ከሆነ በእነሱ የተነሣ ስንቱ ሊቅ ቀውሷል፣ ስንቱም አሰላሳይ ከዘመድ ከወዳጅ ተለይቶ መንኖላቸዋል መሰላችሁ፤ ጥበብን ማፍቀር አያድርስባችሁ እቴ! (እንቢ ካላችሁም የጥበብ ስቃይን ይጣልባችሁ ብሎ መርገም ይቻላል!)
ያሳቢዎቹን ምጥቀት የፈተነውስ ጥበባዊ ፍቅሯ አይደል! ስለዚህ መምህሬም ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ሲል የፍቅርንና የጥበብን ምንነት ያውቃል ማለት ነው፤ ስለዚህ እኔ ያልገባኝ ‹ፍቅር ራሱ ምንድን ነው? ጥበብስ ለምን ልትፈቀር ቻለች?› አልኩት! እሱም በገፅታው ‹ደደብ!› እያለ በቃላት ተረከልኝ! ትንሽ አሰላስሎም ገለጻውን ‹ፍቅርን› ሊተረጉም በመሞከር ጀመረ!
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jun 27, 2014

በሀልዎተ-እግዚአብሔር ዙሪያ በሻይ ቤት የተደረገ ሙግት

ZETOBIA | Friday, June 27, 2014
      (በካሣሁን ዓለሙ)


አንድ ቀን ፒያሣ በሚገኝ አንድ ኬክ ቤት ውስጥ የሃይማኖት መጽሐፍ እያነበብኩ ቁጭ ባልኩበት አንድ ዕድሜው በ20ዎቹ መጀመሪያ የሚገኝ ወጣት አጠገቤ መጥቶ በመቀመጥ ጨዋታ ጀመረ፡፡ የማነበውንም መጽሐፍ ‹እስቲ ልየው› ብሎኝ አሳየሁት፡፡ ከመጽሐፉ ጋር ተያይዞ ባነሳቸው ጥያቄዎችና ነቀፌታዎች የተነሳ የሚከተለውን ክርክር ተጨቃጭቀን ተለያየን፡፡
ልጁ ክርክሩን የጀመረውም “አሁን ይህንን መጽሐፍ ብለህ ታነባለህ?” በሚል ነበር፡፡
እኔም ተናድጄ “ለምን አላነበውም መጽሐፍ አይደለም?” ብዬ በጥያቄ መለስኩለት፡፡
“ማለቴ በዚህ መጽሐፍ ጊዜህን ከምታባክን ለምን የተሻለ እውቀት ያላቸውን መጻሕፍት አታነብም?”
“ምን ዓይነት መጻሕፍት ናቸው የተሻለ ዕውቀት ያላቸው?”
“ለምሳሌ የፍልስፍና መጻሕፍትን አታነብም? ሰዎች ለጥቅማቸው ሲሉ እግዚአብሔር ፣ ሰይጣን፣ ኃጢያት፣ ጽድቅ፣ ኩነኔ ምናምን እያሉ የጻፉትን ተረታተረት ከምትለቃቅም?” አለኝ እያጣጣለ፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jun 23, 2014

ኦክስፎርድ፡ ኢትዮጵያ ከዓለም 2ኛዋ ድሃ አገር ናት

Geez Bet | Monday, June 23, 2014
ኢትዮጵያ ከ108 የዓለም ሃገራት በድህነት ከአፍሪካዊቷ ሃገር ኒጀር ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ  የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ያመለከተ ሲሆን የኢኮኖሚ  ባለሙያዎች ሃገሪቷ ድሃ መሆኗ የሚስተባበል አይደለም ብለዋል፡፡
ሰሞኑን  ዩኒቨርሲቲው ይፋ ባደረገው የጥናት ውጤት፤ በኢትዮጵያ ከሚኖሩ ዜጎች 76 ሚሊዮን ያህሉ ድሆች ሲሆኑ በድሆች ብዛትም ከህንድ፣ ከቻይና፣ ከባንግላዴሽና ፓኪስታን ቀጥሎ ኢትዮጵያ  በ5ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ብሏል፡፡
የድህነት መጠኑን በመቶኛ ስሌት ያስቀመጠው ጥናቱ፤ ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ህዝቧ 87.3 በመቶው ድሃ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 58.1 በመቶው ለኑሮው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ያልተሟሉለት ምስኪን ተመፅዋች ዜጋ ነው ብሏል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የአገራትን የድህነት ደረጃ የለካው የትምህርት፣ የጤናና የኑሮ ሁኔታዎችን መሰረት ያደረጉ አስር መስፈርቶችን  በመጠቀም ሲሆን፣ በአገሪቱ በገጠር ከሚኖረው ህዝብ 96.3 በመቶው፣ ከከተማ ነዋሪው ደግሞ 46.4 በመቶው  በድህነት አረንቋ ውስጥ እንደሚኖር በሪፖርቱ  ተመልክቷል፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jun 2, 2014

ሃይማኖታውያን ያልሆኑ የግእዝ ጽሑፎች (ግንቦት 2006 ዓም አኩስም ትግራይ)

Geez Bet | Monday, June 02, 2014
በዳንኤል ክብረት: -
ክፍል አንድ
1.1 አጠቃላይ የግእዝ ሥነ ጽሑፋዊ ሀብት
የግእዝ ቋንቋ ከሁለት ሺ ዓመታት በላይ ጊዜ ያስቆጠረ የሥነ ጽሑፍ ሀብት ያለው ቋንቋ ነው፡፡ እስካሁን የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የግእዝ ሥነ ጽሑፍ በተጻፉበት ቁስ በሦስት መልኮች ቀርበዋል፡፡ በድንጋይ ላይ፣ በብራና ላይና በወረቀት ላይ፡፡
  1. የድንጋይ ላይ ጽሑፎች፡- በድንጋይ ላይ የተጻፉት የግእዝ ሥነ ጽሑፎች በአኩስም አካባቢ የተገኙትንና የነገሥታቱን የጦርነት ታሪኮችንና ሌሎች ዘገባዎችን የያዙትን ጽሑፎች ይመለከታል፡፡  የተገኙት የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ከአራተኛው መክዘ(ቅልክ) እስከ 8ኛው መክዘ(ድልክ) የሚደርሱ ናቸው፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ ጥንታዊው የሚባለው የድንጋይ ላይ ጽሑፍ በመጣራ ኤርትራ በሐውልቲ የተገኘው(5ኛው መክዘ ቅልክ) ጽሑፍ ነው፡፡
‹ዝ ሐውልት ዘአገበረ
አገዘ ለአበዊሁ ወሰ
ሐበ ሙሓዛተ አውዐ
አለፈነ ወጸበለነ›› የሚለው ነው፡፡
እነዚህ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች አብዛኞቹ ዘገባዎችና ታሪኮች ሃይማኖታውያን አይደሉም፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

በማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ፤ የሲኖዶስ ጉባኤ በፓትርያርኩና ጳጳሳቱ ፍጥጫ ተቋጨ

Geez Bet | Monday, June 02, 2014
ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው፦
ጳጳሳት የፓትርያርኩን የማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ማሻሻያ ቅድመ ኹኔታ አልተቀበሉትም:: 
‹‹ቅድመ ኹኔታው የማኅበሩን አገልግሎት የሚያቀጭጭና በሒደትም የሚያስቆም ነው›› /ታዛቢዎች/- 
የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅን እንደ አንድ አጀንዳ የያዘው የዘንድሮው የሲኖዶሱ የርክበ ካህናት ጉባኤ ከረቂቁ ጋር በተያያዘ በፓትርያርኩና በሊቃነ ጳጳሳቱ መካከል በተፈጠረ ፍጥጫ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
የፍጥጫው መንሥኤ፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተሠየመው የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ አጥኚ ኮሚቴ ያዘጋጀው የማሻሻያ ረቂቅ በዝርዝር ከመታየቱ አስቀድሞ ፓትርያርኩ ለውይይቱ እንደ ቅድመ ኹኔታ ያቀረቧቸው ነጥቦች በአብዛኛው የጉባኤው አባላት የገጠመው ተቃውሞ እንደኾነ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

May 19, 2014

ለፓትርያርኩ እንደራሴ እንደሚመደብ የሚገልጽ የሕግ ረቂቅ ለውይይት ቀረበ

Geez Bet | Monday, May 19, 2014


  • • ‹‹የፓትርያርኩን ሥልጣን ይገድባል›› በሚል ተተችቷል
  • ‹‹አመራራቸውን በብቃት እንዲያከናውኑ የሚያግዝ ነው›› /የሕግ ረቂቁ/
  • ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የሚያስተላልፉት በብሔራዊ ቋንቋ ብቻ ይኾናል:: 

  • ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዕድገትና ነባራዊ ኹኔታዎች ጋራ በማገናዘብ ያሻሽላል የተባለው የሕግ ረቂቁ ለውይይት የቀረበው፣ ባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በመካሔድ ላይ በሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶሱ ኹለተኛ ዓመታዊ መደበኛ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጎች ኹሉ የበላይ ነው የተባለው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቁ÷ ርእሰ አበውና ለካህናቷና ለምእመናንዋ ኹሉ መንፈሳዊ አባት ለኾኑት ለፓትርያርኩ እንደራሴ እንደሚሾም በአንቀጽ 24 ላይ ማስፈሩ ተመልክቷል፡፡ እንደራሴው ‹‹ቅዱስ ፓትርያርኩ ከቤተ ክርስቲያን የተጣለበትን ሓላፊነትና መንፈሳዊ አመራር በሚጠበቀው ብቃትና ደረጃ ለማከናወን እንዲችል የሚያግዝ›› መኾኑ በሕግ ማሻሻያ ረቂቁ ተገልጧል፡ ፡

  •        የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ ፓትርያርኩን የሚያግዝ እንደራሴ እንደሚመደብ በሚገልጽና የፓትርያርኩን ሓላፊነትና ተጠያቂነት በጉልሕ የሚያሳዩ አንቀጾችን ባካተተ የሕግ ረቂቅ ላይ እየተወያየ እንደኾነ ተገለጸ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ በ1991 ዓ.ም. ያወጣችውን ሕግ ከሌሎች ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ጋር በማጣጣም፣
  • እንደራሴው የሚመደበው የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ብቻ በሚሳተፉበት ምርጫ ሲኾን፣ ለምርጫው ሦስት ዕጩዎች በፓትርያርኩና በቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ጥቆማ እንደሚለዩ ተጠቅሷል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖት፣ ቀኖናና ትውፊት የማስጠበቅ እንዲሁም ያለአድልዎ የማስተዳደር ሓላፊነት ላለበት ለፓትርያርኩ በእንደራሴነት የሚመረጠው ሊቀ ጳጳስ ማሟላት የሚገባው መመዘኛ በሕጉ መመልከቱ የተጠቆመ ሲኾን መመዘኛው ለእንደራሴው ከ50 - 60 ዓመት የዕድሜ ገደብ ሲያስቀመጥ፣ የአስተዳደር ችሎታና የመንፈሳዊ አመራር ልምድን፣ መንፈሳዊና ዘመናዊ ዕውቀት አጣምሮ መያዝን እንደሚጠይቅም ታውቋል፡፡ ‹‹ግለሰባዊ የሥልጣን ፈላጊነት ስሜት የሚገንበት፣ የፓትርያርኩን ሥልጣን የሚጋፋና መካሠስን የሚያበረታታ ነው›› በሚል አንቀጹን የተቃወሙ የቤተ ክህነት ሓላፊዎች፣ ምደባው አስፈላጊ ኾኖ ከተገኘም እንደራሴው በፓትርያርኩ ጥቆማ ብቻ መመረጥ እንዳለበት የቃሉ ትርጉም እንደሚያስገደድ በመጥቀስ ይከራከራሉ፡፡
    የአህጉረ ስብከት የሥራ ሓላፊዎች በአንጻሩ፣ የእንደራሴው ምደባ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና ብልሹ አሠራር እንዲታረም የአደረጃጀትና የአሠራርለውጥ ጥናት በማድረግ ላይ ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አመራር መጠናከር የራሱ አስተዋፅኦ አለው በሚል እንደሚደግፉት ተናግረዋል፡፡ እንደራሴው ፓትርያርኩን ከማገዝ ውጭ ‹‹ለቅዱስ ፓትርያርኩ ከተሰጡት ተግባራት ውስጥ የሚጋራው የተለየ ሓላፊነት አይኖረውም፤›› በሚል በረቂቁ የሰፈረውን አንቀጽ በመጥቀስ ምደባው ፓትርያርኩን የመጋፋት ሚና እንደሌለውም ገልጸዋል፡፡ ተጠያቂነትን በተመለከተም ፓትርያርኩን ብቻ ሳይኾን ኹሉንም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት ለቅዱስ ሲኖዶስ ተጠሪ ከማድረግ፣ በአስተዳደር በደልና በአመራር ጉድለት የካህናቱንና የምእመናኑን አመኔታና ተቀባይነት ማጣትን ጨምሮ ከሀብትና ንብረት ባለቤትነት ጋራ የተያያዙ ዝርዝር የተጠያቂነት አንቀጾች በረቂቁ በመካተታቸው በፓትርያርኩ አልያም በወቅታዊ እይታ ላይ ብቻ የታጠረ ረቂቅ እንዳልኾነ ያስረዳሉ፡፡
    ጉዳዩ በዋናነት የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ አመራር ከማጠናከር አንጻር ሊታይ ይገባል የሚሉ አስተያየት ሰጭዎች፣ ምልዓተ ጉባኤው የሕግ ማሻሻያ ረቂቁን በጥልቀት በማዳበር የቅዱስ ሲኖዶሱ ሉዓላዊ ሥልጣን በማንም የማይገሠስበት መሣርያ አድርጎ እንደሚያጸድቀው እንጠብቃለን ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል፣ ፓትርያርኩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታላላቅ በዓላት ላይ እንዳስፈላጊነቱ እየተገኘ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የሚሰጠው እንዲሁም በብዙኃን መገናኛ መንፈሳዊ መልእክት የሚያስተላልፈው በአገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ ብቻ እንደሚኾን በሕግ ማሻሻያ ረቂቁ ላይ መስፈሩ ተጠቅሷል፡፡
  • Source: Addis Admass

ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 2, 2014

የአድባራት አስተዳዳሪዎች ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት መፈረጃቸው ሊቃነ ጳጳሳቱን አስቆጣ

Geez Bet | Wednesday, April 02, 2014
ቅሬታቸውን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ገልጸዋል
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ በኾኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዐት እንዲማሩ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በማቀናጀት ሞያዊ ድጋፍ እንዲያበረክቱ በማስተባበር ላይ የሚገኘውን ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት በመፈረጅ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካይነት ጠቅላላ ሀብቱና ንብረቱ የሚታገድበት ውሳኔ እንዲተላለፍ በመንግሥትም በኩል እርምትና ርምጃ እንዲወሰድበት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአድባራት አስተዳዳሪዎች መግለጫ አውጥተውበታል በተባለው ስብሰባ ጉዳይ ኹለት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ለከፍተኛ የመንግሥት ሓላፊዎች ቅሬታቸውን ማሰማታቸው ተገለጸ፡፡

የቅ/ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስንና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን በስም የጠቀሱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች፣ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች እንደኾነ ቢገልጹም የሓላፊዎቹን ስም ከማሳወቅ ተቆጥበዋል። 
ቤተ ክርስቲያኒቱ በፀረ ሙስናና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከመንግሥት ጋራ የተጠናከረ ሥራ ለመሥራት በቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መወሰኗን ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውሰው፣ በዚህም መሠረት ለሙስናና ብክነት
ሙሉውን አንብብ-Read More

Mar 15, 2014

“ቅዱስ ኤልያስ ይዞት የመጣውን መፅሐፍ” ቤተ ክርስትያን እንድትቀበል ተጠየቀ

Geez Bet | Saturday, March 15, 2014
መጽሐፉ ለአቡነ ማትያስና ለጠ/ሚ ኃይለማርያም እንዲደርሳቸው ተደርጓል
ደብዳቤው ለእስራኤሉ ጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታናሁ እና ለተመድ ተልኳል

       ከተፃፈ ከ2 ሺህ ዓመታት በላይ አስቆጥሯል የተባለውንና ስለ ቅዱስ ኤልያስ መምጣት ምስጢር የሚተነትነውን መጽሐፍ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተቀብላ ወደተለያዩ ቋንቋዎች በማስተርጎም ምዕመናኖችን እንድታስተምር፣ “ማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ” ለቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በጻፈው ደብዳቤ ጠየቀ፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Mar 10, 2014

ፓትርያርኩ ‹‹ቤተ ክርስቲያን በዩኒቨርስቲ ምሩቃን አትመራም” ማለታቸው ቅሬታ ፈጠረ

Geez Bet | Monday, March 10, 2014
ስለማኅበራት የሰጡትን አስተያየት መልሰው እንዲያጤኑት ተጠየቀ
‹‹ማኅበራት በትኩረት ሊመሩና ጉዟቸውም እየተፈተሸ ሊስተካከል ይገባል›› - መንግሥት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ‹‹ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ቤተ ክርስቲያንን እንምራ እያሉ ነው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊትና ሥርዓት አላት፤እንዲህ ማለት አይችሉም›› በማለት የሰጡትን አስተያየት መልሰው እንዲያጤኑት በንግግራቸው ቅር የተሰኙ የመንፈሳውያን ማኅበራት አገልጋዮች ጠየቁ፡፡
አገልጋዮቹ ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፣ አቡነ ማትያስ ይሄን አስተያየት የሰነዘሩት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ከኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ጋር በመተባበር የካቲት 21 እና 22 ያዘጋጁት ሀገር አቀፍ የስብከተ ወንጌል የምክክር ጉባኤ በተካሔደበት ወቅት ነው፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jan 18, 2014

ጥምቀት በአዲስ አበባ

Geez Bet | Saturday, January 18, 2014
ከ123 አብያተ ክርስትያን የሚወጡ ታቦታት በ46 ጥምቀተ ባሕሮች ያድራሉ
በየዓመቱ በኢትዮጵያ የሚከበረው የጥምቀት በዓል በሀገሪቱ ውስጥ በጐዳናና በአደባባይ ከሚከናወኑ በዓላት አንዱ ነው፡፡ አንዲት የውጭ ሀገር ዜጋ በአንድ ዘመን ይህን በዓል ከተመለከተች በኋላ፤ “በየትኛውም ሀገር የሚከበር ካርኒቫል የማይተካከለው፣” ስትል አድንቃ ጽፋለች።
ይቺ ጸሓፊ በብራዚል ዘመን መለወጫ ላይ የሚፈፀመውን ካርኒቫል ጭምር በመጥቀስ ነበር የጥምቀቱን አቻ የለሽነት የገለጠችው፡፡ አውሮጳዊቷ ጥምቀትን የተመለከተችው አዲስ አበባ ላይ ነበር፡፡ የጥምቀትን በዓል የደመቀና ቀለማም የሚያደርገው ከአከባበሩ ሥነሥርዓት ጋር በዓሉ የሚከናወንበት ቦታም የራሱ ድርሻ ይኖረዋል። በከተማና በገጠር ያለው አከባበር
ሙሉውን አንብብ-Read More

ፓትርያርኩ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በሙስና ላይ እንዲዘምቱ አዘዙ

Geez Bet | Saturday, January 18, 2014
“በቤተክርስትያናችን ሽፍጥና ጉቦ ተንሰራፍቷል”
ሰንበት ት/ቤቶቹ የአማሳኝ አስተዳዳሪዎችን ዶሴ ለፓትርያርኩ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በተንሰራፋው ሙስናና ሸፍጥ ላይ በተጠናከረ ኃይል በመዝመት የተጀመረውን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ከዳር እንዲያደርሱ አዘዙ፡፡ አቡነ ማትያስ ትእዛዙን የሰጡት ሙስናና ብልሹ አስተዳደርን በሥር ነቀል የእርማት
ርምጃዎች ለማስተካከል ያስተላለፉትን መግለጫ ለመደገፍና የፓትርያርኩ ልዩ ሀ/ስብከት የኾነው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ያዘጋጀው የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት ተግባራዊ እንዲኾን ለመጠየቅ ከትላንት በስቲያ ኀሙስ፣ ጥር 8 ቀን 2006 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ለተሰበሰቡት በሺሕ ለሚቆጠሩ የሰንበት ት/ቤት
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jun 11, 2013

የፓን አፍሪካኒዝም ራዕይ ጭንገፋ!

Geez Bet | Tuesday, June 11, 2013

              ክፍል አንድ 
W. E. B. Du Bois
 ምዕራባዊያን አፍሪካን በበጎ ነገር አያነሷትም፡፡ የቀደምት ስልጣኔዋንም አምነው አይቀበሉትም፡፡ አፍሪካዊያኑም ቢሆኑ ስለማንነታቸውና ስለታሪካቸው ያላቸው እውቀት ፈረንጆች አፍሪካን ከሚያውቋት እጅግ ያነሰ ነው፡፡ ይህ ነገር ደግሞ አሁን አፍሪካ ካለባት ችግር በተጨማሪ ነገሩ የገለባ እሳት ሆኖባታል፡፡ አፍሪካ ባንድ ወቅት ኃያል ሃገር ነበረች፡፡ ነገር ግን ስልጣኔዋ ተሸመደመደና ወደ ጨለማው ዘመን ገባች፡፡ የስልጣኔ መሽመድመድ በታሪክ አፍሪካ ብቻ ሳትሆን አውሮፓንም ደቁሷታል፡፡ ምስጋና ይግባቸውና የሰሜን አፍሪካ ሙሮች (Moors) በሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ አውሮፓ ተሻግረው፣ ጨለማ ውስጥ የምትገኘውን አህጉር አቀኑ፡፡ ከዚያ በኋላ አውሮፓ ሰለጠነችና አፍሪካን ተቀራመተች፡፡ ይህንን የአፍሪካ ቅርምጥ የአብርሆት (Enlightenment) ዘመን ልሂቃን የሚባሉት ጭምር ደግፈውታል፡፡ የአፍሪካ ህዝብ ሰብአዊ መብቱ ተገፎ ሰው ያለመሆኑ ታወጀ እና ለባርነት ተጋዘ፣ ተገረፈ፣ ተሰቃየ፣ ተሰቀለ፣ ታደነ፣ ታነቀ፣ ተገደለ፣ ንብረቱ ተዘረፈ፣ የአገር ባለቤትነቱን ተነጠቀ፣ ሳይፈልግ የወራሪዎቹን ባህል፣ ትምህርት፣ ኃይማኖት እንዲቀበል ተገደደ ………. ምን ያልሆነው አለ? እናም ይሄንን ግፍ አሽቀንጥረው ለመጣል ሃሳብ ያላቸው ጥቁር ልሂቃን በየቦታው ማኮብኮብ ጀመሩ፡፡ በመጀመሪያ ሰለ እነዚህን ንቅናቄዎች እና ኢትዮጵያኒዝም ትንሽ እንመለከታለን፡፡ ከዚያም ወደ ፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ እና ዓላማ፣ በመጨረሻም የፓን አፍሪካኒዝም ራዕይ እንዴት በአፍሪካዊያን አምባገነን መሪዎች እንደጨነገፈ
ሙሉውን አንብብ-Read More