Time in Ethiopia:

Showing posts with label Amharic. Show all posts
Showing posts with label Amharic. Show all posts

Dec 24, 2014

የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና – ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ከዝዋይ እስር ቤት)

Geez Bet | Wednesday, December 24, 2014
በእስር ላይ ያለው የተደናቂው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሁለተኛውንና ‹የኢትዮጵያ መንግስት ገበና› የተሰኘው ጦማር ከዝዋይ እስር ቤት ወጥቷል፡፡ ተመስገን አብረውት የታሰሩ የፖለቲከኛ እስረኞች በሚታወቅበት የጋዜጠኝነት ችሎታው እየጠየቀና እያውጣጣ መፈጠራቸው የሚያስምሙ ታሪኮችን ለመልቀም እንደቻለ ጽሁፉን ያነበበ ይረዳዋል፡፡
ክፍል 2
ተመስገን ደሳለኝ
በዚህ አውድ ለማቅረብ የተገደድኩበትን ዘግናኝ ታሪክ፣ ወደር በሌለው አስከፊነቱ የተነሳ ለንባብ ባላበቃው በወደድኩ ነበር፡፡ ግና! ይህ መንግስታዊ የጭካኔ ተግባር፣ ዛሬም በምስኪን ዜጎች ላይ እየተፈፀመና ብዙዎችን ሰለባ እያደረገ በመሆኑ ህዝቡ ይህን ሊሸሸግ እየተሞከረ ያለውን መከራ ተረድቶ ሥርዓቱን በአደባባይ ዓመፅ “ሃይ!” ይል ዘንድ ትርክቴን ለማጠናቀር ተገድጄያለሁ፡፡ ለእስር ያበቃኝ የጋዜጠኝነት ሙያዬም ተጨማሪ ዕዳ ጭኖብኛል፡፡


“ጄል-ኦጋዴን”
ጄል ኦጋዴን በሱማሌ ክልል ርዕሰ-መዲና የሚገኝ፤ ለ800 እስረኞች ታቅዶ በ1992 ዓ.ም የተገነባ እስር ቤት ነው፡፡ የግቢውን ዙሪያ ከከበበው አጥር በግምት 15 ሜትር ፈንጠር ብሎ ሌላ ተደራቢ የድንጋይ አጥር ተበጅቶለታል፡፡ እስከ ሚያዝያ 24 1999 ዓ.ም ድረስ እስር ቤቱ በሌሎች የሀገሪቱ
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 23, 2014

የሕወሓት አስተዳደር የአስመራው መንግስት ሄሊኮፕተሩን በሱዳን በኩል እንዲመልስለት መጠየቁ ተሰማ

Geez Bet | Tuesday, December 23, 2014
(ምንሊክ ሳልሳዊ) ስርአቱን ከዱ የተባሉት አብራሪዎች ከድሬዳዋ ተነስተው በጅቡቲ ድንበር አስታከው በአሰብ ዘልቀው ኤርትራ ያሳረፉት ሄሊኮፕተር በሱዳን በኩል እንዲመለስለት ሻእቢያን መጠየቁን የሱዳን ዲፕሎማቶች ጠቆሙ::
ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርገውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በአየር ሃይሉ ውስጥ የሚፈጸመውን ደባ በመቃወም ከድተዋል የተባሉት 2 ፓይለቶች(ካፒቴን ሳሙኤል እና ቢሊሊኝ )እና አንድ ቴክኒሽያን(ጸጋ ብርሃን)ለኤርትራ መንግስት እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ይህንንም የወያኔው ቴሌቭዥን ጣቢያ እማኝነቱን ሰቷል::
አብራሪዎቹ ይዘውት የሄዱትን ሄሊኮፕተር እንዲመለስለት ወያኔ የሱዳን ዲፕሎማቶችን የላከ ሲሆን ሻእቢያ የማይመልስ ከሆነ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ከባድ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አንድ ለስርአቱ ቅርብ የሆነ ድህረገጽ ጽፏል::
በሃገር ውስጥ እና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ፖለቲካ ድል ሲቆጥሩት አንዳንዶቹ ወያኔ የሻእቢያን አየር ሃይል በሰው ሃይል እየገነባ ሊሆን ይችላል ከጀርባ ሌላ ደባዎች በወያኔ እና ሻእቢያ ሊሰራ ይችላል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አልጠፉም::የወያኔ መክላከያ ሰራዊት አጸፋዊ እርምጃ ይወስዳል የሚል ስጋት ቢያይልም;ሃገር ወዳዶች ግን ምንም እርምጃ አይወስድም የፍርሃት ዛቻ ነው ሲሉ ተደምጠዋል::
ሙሉውን አንብብ-Read More

Oct 9, 2014

‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ብሎ ለጠየቀ!

ZETOBIA | Thursday, October 09, 2014

(በካሣሁን ዓለሙ)

‹ፍልስፍናን እማራለሁ› ብዬ ት/ቤት ብገባ፣ መምህሩ ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ብሎ መልሶ እኔኑ ጠየቀኝ፤ ‹ካወቅኳትም ለም
ንስ ልማራት ሒሳብ ከፈልኩ?› አልኩኝ፤ ምን ላድርግ? ቢቸግረኝ ያው ‹የፍልስፍና አስተማሪዎች ናቸው› ከሚባሉት ፋይል የሰማሁትን ስምምነታቸውን ይዤ፡- ፍልስፍና እኮ እንዲህ ነው ማለት ጀመርኩ!
በመሠረቱ ጭንቁ መልሱ ላይ ነው እንጂ የፍልስፍና አዋቂና ምጡቅ የተባለ ሁሉ ይችን ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› የምትል ጥያቄ ሳያነሳት አይቀርም፤ መምህሬም ‹ጥያቄዋ ትንሽ ገብታው ነው› መሰል የጠየቀኝ፤ እንደኔ ያላብላሉት ሳይሆኑ መልሷን ሲጭሩ የኖሩት ሊቃውንት ግን ግምታዊ መልሳቸውን ሰጥተዋል፤ እኔም በመጠኑ ሰምቻለሁ (ከፈለጋችሁ ጆሮ ጠገብ በሉኝ)፡፡ በአጠቃላይ ግን በሊቃውንቷ ‹ፍልስፍና ጥበብን ማፍቀር ናት› የሚል ስምምነት ላይ ተደርሶባታል ብሏል መምህሬ ራሱ፡፡ እንደዚህ ከሆነማ ማጠንጠኛዎቿ እነዚህ ‹ጥበብ› እና ‹ፍቀር› የሚሉ ቃላት (ጽንሣተ-ሐሣብ) ናቸው ማለት ብዬ ያዝኩ፡፡ እነዚህ ሁለት ቃላት ደግሞ ዓለምን በመሠረትነትና በዓምድነት (ምሠሦ ሆነው) ያቆሙ ኃይላት ናቸው፡፡ የፍልስፍናም ድንቅነት የተመሠረተው በእነሱ የውህድነት ጥንጣኔ ላይ ሊሆን ነው፡፡ መምህሬም ጥያቄዎቹን አከታተለ ‹እንዴት ተዋሃዱ? የውህደታቸው ጥብዓትስ እስከምን ድረስ ነው? በምን ያህል አስተውሎትስ ልንረዳቸው ቻልን? የእሴትና የኪን (የውበትን) ተውህቦስ ማን አደላቸው? ነው በራሳቸው በሌጣነት ነው አንክሮ ውስጥ የከተቱን?› የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እያነሳ አስጨነቀን! እንደተረዳሁት ከሆነ በእነሱ የተነሣ ስንቱ ሊቅ ቀውሷል፣ ስንቱም አሰላሳይ ከዘመድ ከወዳጅ ተለይቶ መንኖላቸዋል መሰላችሁ፤ ጥበብን ማፍቀር አያድርስባችሁ እቴ! (እንቢ ካላችሁም የጥበብ ስቃይን ይጣልባችሁ ብሎ መርገም ይቻላል!)
ያሳቢዎቹን ምጥቀት የፈተነውስ ጥበባዊ ፍቅሯ አይደል! ስለዚህ መምህሬም ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ሲል የፍቅርንና የጥበብን ምንነት ያውቃል ማለት ነው፤ ስለዚህ እኔ ያልገባኝ ‹ፍቅር ራሱ ምንድን ነው? ጥበብስ ለምን ልትፈቀር ቻለች?› አልኩት! እሱም በገፅታው ‹ደደብ!› እያለ በቃላት ተረከልኝ! ትንሽ አሰላስሎም ገለጻውን ‹ፍቅርን› ሊተረጉም በመሞከር ጀመረ!
ሙሉውን አንብብ-Read More

Aug 8, 2014

አገሬ ታማለች!

ZETOBIA | Friday, August 08, 2014

አገሬ ታማለች!


(በካሣሁን ዓለሙ)
እማማ ታማለች፣
አገሬ ታማለች፣
ሆስፒታል ተኝታ
እ!እ!…ህእ!ም!…ህም!!! ትለኛለች፤
ከህቅታዋም ውስጥ ጣሯ ይሰማኛል፣
ህመሟን ስቃዩዋን፣
ዝም ብዬ እየሰማሁ፣
እማዬ! እላታለሁ፤
ህመሟ ያመኛል፣
ጧሯ ይነዝረኛል፣
አዎ! እማማ ታማለች፣
ይኸው በሆስፒታል
እ!!…ህ!!!.. እህ!!!… ትለኛለች፤
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jul 14, 2014

የአንዳርጋቸው ጽጌ የእንግሊዝ ፓስፖርት

Geez Bet | Monday, July 14, 2014
ማክሰኞ ምሽት ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ኢቲቪ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አስመልክቶ ያቀረበው ዜናን ብዙዎች በተቀላቀለ ስሜት ነበር የተከታተሉት፡፡
ዜናው የአቶ አንዳርጋቸውን ንግግር ለአፍታ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱ ግን ግራ ያጋባቸው በርካቶች ናቸው፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ‹‹እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ፡፡ እውነቴን ነው የምልህ እኔ እንደ ምርቃት ነው የተቀበልኩት፡፡ አሁን የሚያስቸኩለኝ ነገር የለም፡፡ ጥሩ ዕረፍት ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ ምክንያቱም በጣም በጣም ደክሞኛል … ሰልችቶኛል፡፡ እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ጥላቻ በውስጤ የለም፡፡ ምንም ዓይነት ብስጭት የለኝም፡፡ ምንም ዓይነት መጥፎ ስሜት አይሰማኝም፡፡ በቃ … የመጨረሻ እርጋታና ዕረፍት ውስጥ ነው ያለሁት፤›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከአንዴም ሁለቴ በፍርድ ቤት በሽብርተኝነት ከሶ የሞት ፍርድ ባስፈረደ መንግሥት ቁጥጥር ሥር የዋለ ሰው በጤናው ደስተኛነቱን አይናገርም የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች፣ የንግግሩን አንድምታ በተመለከተ የተራራቀ መላምታቸውን ማቅረባቸውን ቀጥለዋል፡፡ ለአንዳንዶች የአቶ አንዳርጋቸው ንግግር ባልተጠበቀ መንገድ በጠላቶቹ እጅ የወደቀ ሰው ያለበትን ሁኔታ ባለመቀበል የሰጡት ነው፡፡ ለሌሎች ደግሞ በአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ ሁኔታ ላይ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እያሰማ ላለው ሥጋት ምላሽ ለመስጠት መንግሥት አስገድዷቸው የሰጡት ቃል ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልገሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረ ኃይል አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሰንዓ በኩል ወደ ኤርትራ ሊገቡ ሲል ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው፣ በዚያው ዕለት ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታ
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jul 8, 2014

ኢትዮጵያውያን ባሎች ሚስቶቻቸውን በመደብደብ ከአፍሪካ 3ኛ ናቸው

Geez Bet | Tuesday, July 08, 2014

87 በመቶ የማሊ ሴቶች ድብደባ ተገቢ ነው ይላሉ:: 
የጊኒና የኢትዮጵያ ሴቶችም ድብደባ ተገቢ ነው ብለው ያስባሉ:: 
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ተቋማት በቤት ውስጥ ጥቃት ዙሪያ ያወጧቸውን ሪፖርቶች መነሻ በማድረግ በቅርቡ በ37 የአፍሪካ አገራት ላይ የተሰራ አንድ ጥናት፣ ኢትዮጵያውያን ባሎች ሚስቶቻቸውን አዘውትረው በመደብድብ 3ኛ መሆናቸውን አረጋገጠ።
‘አፍሪካ ሄልዝ፣ ሂዩማን ኤንድ ሶሻል ዲቨሎፕመንት ሰርቪስ’ የተባለው አህጉራዊ ድርጅትና በሴቶች ጥቃት ዙሪያ የሚሰሩ ሌሎች ተቋማት በጋራ የሰሩት ጥናት እንደሚለው፣ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ባሎች የትዳር አጋሮቻቸውን መደብደብ አግባብ ነው ብለው የሚያስቡና በተለያዩ ምክንያቶች ሚስቶቻቸውን የሚደበድቡ ናቸው፡፡ 
ጥናቱ ከተሰራባቸው የአፍሪካ አገራት የበለጠ ተደባዳቢ ባሎች ያሉባት አገር ናት ተብላ በቀዳሚነት የተቀመጠችው ኡጋንዳን ስትሆን፣ ሴራሊዮን ሁለተኛ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ ሶስተኛ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jul 7, 2014

ድኻው ምን አረገ

Geez Bet | Monday, July 07, 2014
ዳንኤል ክብረት: -
ሰሞኑን ከአንድ ሰው ‹የማጭበርበር› ነገር ጋር በተያያዝ ከዚህም ከዚያም አስተያየት ይሰጣል፡፡ አብዛኞቹ የመገናኛ ብዙኃንም ትኩረታቸውን በሰውዬው ላይ አድርገው እንዴት እንዲህ ሊያደርግ ቻለ? ለምን እንዲህ አደረገ? ምን ነክቶት ነው? እያሉ ጉዳዩን ከማኅበረሰብ ሳይንስ፣ ከሥነ ልቡና፣ ከእምነትና ከባሕል አንጻር እየተነተኑ ይገኛሉ፡፡
እኔ ግን ይህን ጉዳይ ስከታተል ትዝ የሚለኝ አንድ የሀገራችን ተረት ነው፡፡ ሰውዬው መንገድ ላይ ሲሄድ በሩ ወለል ብሎ የተከፈተ ቤት ያገኛል፡፡ ለጥቂት ቆም ብሎ ሁኔታውን ሲያይ ማንም በአካባቢው ዝር የሚል አልነበረም፡፡ ነገሩ የተከፈተ በር ብቻ ሳይሆን ‹የተከፈተ ዕድልም› የሆነለት ሰውዬ የተከፈተው ቤት ውስጥ ዘው ብሎ ይገባል፡፡ማንም አልነበረም፡፡ ወዲያና ወዲህ እየተንጎራደደ ቤቱን ቃኘና ዓይኑ ያረፈበትን ዕቃ ይዞ ላጥ አለ፡፡ መንገድ ላይ ያዩት ሰዎች የሚያውቁትን ዕቃ አንድ ሰው ይዞ ሲሸመጥጥ በማየታቸው ይጠራጠሩና ያስቆሙታል፡፡ ፖሊስም በነገሩ ይገባበታል፡፡ ሰውም ከዚህም ከዚያም ይወርድበታል፡፡
      ግርግሩ በዚህ መልክ እየቀጠለ ዕቃቸው የተሰረቀባቸው ሰዎች ኡኡ እያሉ ይደርሳሉ፡፡ ሲደርሱም የቤት ዕቃቸው በአንድ በማያውቁት ሰው ትከሻ ላይ ያገኛሉ፡፡ ግርግሩን ሰንጥቀው ይገቡና ‹‹ሞላጫ ሌባ›› እያሉ ሌባውን በጥፊ ሲመቱት ሌባው ተናድዶ ዕቃውን ያወርድና ጥፊውን በጥፊ ይመልሳል፡፡ ፖሊስ በድርጊቱ ተገርሞ ከዚያ ሁሉ ሰው ይልቅ ለባለቤቶቹ ጥፊ ለምን መልስ እንደሰጠ ሲጠይቀው ‹‹ቤታቸውን ከፍተው እየሄዱ ሰው ሌባ ያደርጋሉ›› አለ ይባላል፡፡
የሰሞኑ ሁኔታም ይህን ነገር እንድናየው የሚያደርግ ነው፡፡ ለመጭበርበርና ለመታለል የሚችል አሠራር፣ አካሄድና አፈጻጸም የዘረጋነው እኛው ነን፡፡ ነገሮችን በመረጃና በማስረጃ ላይ ተመርኩዘን ከመወሰን ይልቅ በሚወራ ወሬ፣ በሚገነባ ገጽታና ከሚዲያ በምንሰማው ነገር ላይ ብቻ የመመራትን አሠራር ያሰፈንነው እኛው ነን፡፡ ዛሬ ቀን ጥሎት የተጋለጠው ሰው ላይ በወደቀ ዛፍ ላይ የሚበዛውን ምሣር ሁሉ እናዘንብበታለን እንጂ ሌሎች ወደፊት እንዳይከሰቱ የሚያደርግ አደረጃጀት፣ አሠራርና አስተሳሰብ ግን አልዘረጋንም፡፡  
ሙሉውን አንብብ-Read More

የእንግሊዝ መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ መተላለፋቸውን መስማቱን አስታወቀ

Geez Bet | Monday, July 07, 2014
-አና ጎሜዝ ወደ እንግሊዝ መመለስ አለባቸው እያሉ ናቸው:: 
ከዱባይ ወደ አስመራ ለመሄድ የመን ሰንዓ ላይ በየመን የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ታስረዋል የተባሉት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ለኢትዮጵያ ተላልፈው ተሰጥተዋል መባሉን እንደ ሰማ የእንግሊዝ መንግሥት አስታወቀ፡፡
ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ማረጋገጫ እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡ 
በአዲስ አበባ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ጸሐፊ ሚስተር ኢያን ኮክስ አቶ አንዳርጋቸውን በሚመለከት ለሪፖርተር በላኩት መግለጫ እንዳስረዱት፣ የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው አቶ አንዳርጋቸው  ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ሰነዓ ውስጥ መጥፋታቸው ተገልጾላቸዋል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የእንግሊዝ ባለሥልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ያሉበትን ሁኔታና ሥፍራ ለማወቅ የየመን ከፍተኛ ባለሥልጣናትንና በእንግሊዝ የሚገኙትን የየመን አምባሳደርን ማነጋገራቸውን አስረድተዋል፡፡
ኢያን ኮክስ አንዳንድ ከሚወጡ መረጃዎች ለመረዳት እንደቻሉት፣ አቶ አንዳርጋቸው ምናልባትም ኢትዮጵያ ውስጥ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ በመሆኑም ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በአስቸኳይ ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባለፈው ዓርብ ባወጣው መግለጫ፣ አቶ አንዳርጋቸው በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ እንደሚገኙ ከሪፖርቶች መረዳት መቻሉን ገልጾ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ማረጋገጫ በአስቸኳይ እንዲሰጠው መጠየቁን አስታውቋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የእንግሊዝ ባለሥልጣናት በእንግሊዝ የየመን አምባሳደርን አነጋግረዋቸው፣ አቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው መሰጠታቸውን ለቤተሰቦቻቸው መንገራቸውን ለቢቢሲ አስታውቀዋል፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jul 2, 2014

የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን በቁጥጥር ሥር ስለመዋላቸው የሪፖርተር ዘገባ

Geez Bet | Wednesday, July 02, 2014
መነሻቸውና መድረሻቸው ከየትና ወዴት እንደሆነ ያልተገለጸው የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ የመን ሰንዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በየመን የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው መታሰራቸው ተሰማ፡፡ 
አቶ አንዳርጋቸው በየመን የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ታስረዋል የተባለው ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ሲሆን፣ ሰንዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከመያዛቸው ውጪ ከየት ተነስተው ወዴት እንደሚሄዱ አልታወቀም፡፡
    በኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ከተፈረጁት አልቃይዳ፣ አልሸባብ፣ ኦነግና ኦብነግ ጋር በአሸባሪነት የተፈረጀው ግንቦት 7 ዋና ጸሐፊውን በሚመለከት ያወጣው መግለጫ እንደሚያስረዳው፣ አቶ አንዳርጋቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ካወቀ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች ለማስለቀቅ ውስጥ ለውስጥ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካለትም፡፡ 
አቶ አንዳርጋቸው በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከአስመራ በየመኒያ አየር መንገድ ተሳፍረው፣ በየመን ሰንዓ ትራንዚት በማድረግ ወደ ኳታር ዶሃ ለመጓዝ ሲሞክሩ ሳይሆን እንደማይቀር የተለያዩ ድረ ገጾች ዘግበዋል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ደርግ የንጉሡን ሥርዓት በኃይል ከተቆጣጠረበት ሁለት ዓመታት በኋላ በ1969 ዓ.ም. ይከታተሉት የነበረውን የምህንድስና ትምህርት አቋርጠው ወደ ትግል መግባታቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jul 1, 2014

የግንቦት 7ቱ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ታሰሩ

Geez Bet | Tuesday, July 01, 2014
የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አባልና በአስመራ የሚገኘውን የግንቦት 7 ትግል ይመሩታል የሚባሉት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታሰራቸውን ግንቦት 7 ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
እንደ ግንቦት 7 ንቅናቄ መግለጫ ከሆነ አቶ አንዳርጋቸው ላለፉት አንድ ሳምንታት በየመን ታግተው የሚገኙ ሲሆን ለማስለቀቅ የተደረገው ጥረትም አልተሳካም። አቶ አንዳርጋቸው ወደ የመን የተጓዙት ለትራንዚት እንደሆነ የገለጸው የንቅናቄው መግለጫ የየመን መንግስት እኚህን የትግል ሰው ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ እንዳይሰጥ ስጋት እንዳለበት አስታውቋል።
በአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ጉዳይ በሶሻል ሚዲያዎች ላይ መነጋጋሪያ የሆነ ሲሆን የፖለቲካ ተንታኙ ጃዋር መሀመድ የሚከተለውን በፌስቡክ አስፍሯል።
Jawar Mohammed On Facebook:
“Despite our difference in political opinion, I am shocked with news of
ሙሉውን አንብብ-Read More

10 የሱዳን ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ተገደሉ

Geez Bet | Tuesday, July 01, 2014
አፍሪካን ፕሬስ ኤጀንሲ እንደዘገበው 10 የሱዳን ወታደሮች በኢትዮ -ሱዳን ድንበር አካባቢ ከተገደሉ በሁዋላ በድንበር አካባቢ ውጥረት ሰፍሯል። እሁድ እለት ደግሞ ተጨማሪ 13 የሱዳን ወታደሮች መቁሰላቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ጥቃቱም በኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች ሳይፈጸም እንዳልቀረ ተዘግቧል።
የሱዳን ኮማንዶ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሃይሉን እያሰባሰበ መሆኑን የገለጸው ዘገባው፣ በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መካሄዱን ጠቅሷል። ሱዳንና ኢትዮጵያ የድንበር ከተሞቻቸውን ከታጣቂዎች ጥቃት ለመከላከል በሚል  አንዱ በሌላው አገር ድንበር ጥሶ በመግባት እርምጃ እንዲወስድ መስማማታቸው ይታወቃል።
የሱዳን መንግስት ወታደሮቹ መገደላቸውን አምኖ፣ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ተገደሉ የሚለውን እንደማይቀበለው አስታውቋል። የሱዳን መንግስት ጦር ቃል አቀባይ ኮሌኔል አልስዋርሚ ካሊድ ሳድ እንደተናገሩት ወታደሮቻቸው የተገደሉት
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jun 30, 2014

ልቃዊነት የዘመናችን ሃይማኖት

ZETOBIA | Monday, June 30, 2014
 ካሣሁን ዓለሙ:-

ሃይማኖት በሥርዎ ቃሉ ማመንና መታመን የሚሉ ፅንሣተ-ሐሣብን የያዘ ቃል ነው፡፡ ማመን በአንድ ነገር ላይ እምነት ማሳደር ሲሆን መታመን ደግሞ ላመኑበት ነገር መታገልና መቆም ነው፡፡ ይህንን ይዘን ወደ ፍልስፍናው መከራከሪያ ስንገባ በዓለማችን የሚገኙ የሃይማኖት ይዘቶችን በሦስት ከፍለን ልንያቸው እንችላለን፡፡
1) በእግዚአብሔር ህልውነት ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት (Theist)
የእግዚአብሔር ህልውነትን በማመንና እሱን በመመሥከር እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ግኑኝነት የሚያደርግ በሥራው ፍፁም የሆነ አምላክ መሆኑን ይቀበላል፡፡ ስለሆነም የሰው ልጆች ከእነሱ በላይና ፍጹም ከኾነ ኃይል ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ፤ እሱም በመገለጥ ስለ ዐለማትና ፍጥረታት አፈጣጠር፣ ስለ ሰው ልጆች መፈጠርና ህልውና ነግሯቸዋል፤ ያነጋግራቸዋል ብሎ ያምና፤ ለዚህም ጥብቅና ቆሞ ይመሠክራል፤ ይከራከራል፡፡
2) በእግዚአብሔር አለመኖር ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት (Atheist)
ይኸ የእግዚአብሔርን ህልውነት የሚክድና ለዚያም አቋም ጥብቅና የቆመ ሃይማኖት መሰል አስተምህሮ ነው፡፡ይህም ሃይማኖት የራሱ መታወቂያ አለው፡፡ በአንድ በኩል ሰይጣንን በግል እያመለከ የእግዚአብሔርን ህልውነት የሚቃወም ሲሆን በአብዛኛው በኢሉምናቲ የሚሥጢር ማኅበራት የሚቀነቀን ነው፤ ምሥጢራዊነቱም ያመዝናል፡፡ ስለዚህ በግልፅና በተቋማዊ አደረጃጀት የማይታወቅ ቢመስልም በአብዛኛው በሳይንስና በፍልስፍና አስተምህሮ ተወሽቆ እምነቱ ተቀባይነት አግኝቶ እንዲስፋፋ ጥረት ይደረግለታል፡፡ የዚህ ሃይማኖት አቀንቃኞች በዋናነትዝግመተ ለውጠኛችና ቁሳካላዊያን ናቸው፡፡ለምሳሌ እንደ ፈርደሪክ ኒቼ፣ ካርል ማርክስ፣ ሌኒን፣ ዳሪዊን፣ ሪቻርድ ዳውኪንስና መሰሎቻቸውን መጥቀስይ ቻላል፡፡
3) ‹አሊለም› (እግዚአብሔር አለ-የለም) ሃይማኖት (Agnostic)
የእዚህ ሃይማኖት መነሻው ልቃዊነት (Liberalism) ማሳለጫው ምንፍቅና (Skeptic) ተግባሩም ውል አልባነትና ግደለሽነት (indifference) ነው፡፡ የመከራከሪያ ስልቱም ዥዋዥዌ መጫወት ነው፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው? (በፐሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም)

Geez Bet | Monday, June 30, 2014
ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤  በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ  የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ ካሣሁን ላይ በተቀነባበረ መንገድ የሚፈፀመው ማሰቃየት ማንንም ሰው የሚያሳስብ ነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።

በቴዎድሮስ ላይ ከባድ ተንኮል ሲፈጸምበት የሰማሁት በመጀመሪያ ዛሬ በስደት ላይ ባለው « አዲስ ነገር» የሚባል ጋዜጣ ላይ ነበር፤ ጋዜጣው ቴዎድሮስ በሙያው ያገኘውን መልካም ስም በሰፊው ጥላሸት ቀብቶት ነበር፤ በጣም ሰፊ የሆነ ሀተታ በቴዎድሮስ ዘፈኖች ላይ በማቅረባቸው ምን ያህል አንገብጋቢ የአገር ጉዳይ አግኝተውበት ይሆን ብዬ አነበብሁት፣ ምንም ለአገር  የሚጠቅም ጉዳይ አላገኘሁበትም፤ በዘፈኖቹ ላይ በተደረገው ሂስም ከጋዜጠኞቹ መሀከል የሙዚቃ ሙያ ባለቤት እንዳለ ብጠይቅም ጋዜጣው ባለሙያ እንደሌለውና ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ባለሙያ ማማከራቸውን ነገሩኝ፣  ስሙ  እንዲጠቀስ የማይፈልግ ባለሙያ፣ ባለሙያ አይባልም፣ እንኳን በሙያው በራሱም አይተማመንም ማለት ነው፤ በዚህ በራሱ በማይተማመን ሰው ምስክርነት ላይ በተመሰረተ ረጅም ነቀፌታ ቴዎድሮስን ደበደቡት፤

ሁለተኛው የቴዎድሮስ ጣጣ በመኪና ሰው ገጭቷል ተብሎ መከሰሱ ነው፤ በሌሊት፣ በጨለማ ነው፤ ቴዎድሮስ እንደሚለው  «እኔ ወደአገሬ የገባሁት ሰውዬው ሞተ በተባለበት ቀን ማግስት እንደሆነ ቪዛዬ ያረጋግጣል፣»  (ነጋድራስ መስከረም 30/2001 ዓ.ም. ) በኋላም ከዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የተገኘው መረጃ ይህንኑ የሚያረጋግጥ እንደነበረ ተነግሮአል፤  በዚሁ በነጋድራስ ጋዜጣ ላይ የሚከተሉት መረጃዎች ተጠቅሰዋል ፦
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jun 29, 2014

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ከግብፅ ፕሬዚዳንት ጋር በሰባት ነጥቦች ላይ ተግባቡ

Geez Bet | Sunday, June 29, 2014
በኢኳቶሪያል ጊኒ ዋና ከተማ በተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ ላይ የተገናኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የግብፅ ፕሬዚዳንት  አብዱልፈታህ አልሲሲ፣ በዓባይ ወንዝ አጠቃቃምና የታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በሰባት ነጥቦች መግባባት ላይ ደረሱ፡፡

የግብፅ ሚዲያዎች መግባባቱን አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ሲሉ፣ አንዳንድ የኢትዮጵያ የውኃ ሀብት ባለሙያዎች ደግሞ የመግባቢያ ነጥብ ቁጥር አምስት ይዘት ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል የሚል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ተገናኝተው ባደረጉት የጎንዮሽ ውይይት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በፀጥታና በአካባቢያዊ ግንኙነቶች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ ኮሚሽን ለመመሥረት ተስማምተዋል፡፡
የዓባይ ወንዝ ለግብፃዊያን የመኖራቸው ወይም የህልውናቸው ጉዳይ መሆኑን፣ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ የልማት ጥያቄ እንደሆነ መግባባታቸውን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡
የዓባይ ውኃ አጠቃቀምን በተመለከተ ባደረጉት ውይይትም በሰባት ነጥቦች ላይ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jun 27, 2014

በሀልዎተ-እግዚአብሔር ዙሪያ በሻይ ቤት የተደረገ ሙግት

ZETOBIA | Friday, June 27, 2014
      (በካሣሁን ዓለሙ)


አንድ ቀን ፒያሣ በሚገኝ አንድ ኬክ ቤት ውስጥ የሃይማኖት መጽሐፍ እያነበብኩ ቁጭ ባልኩበት አንድ ዕድሜው በ20ዎቹ መጀመሪያ የሚገኝ ወጣት አጠገቤ መጥቶ በመቀመጥ ጨዋታ ጀመረ፡፡ የማነበውንም መጽሐፍ ‹እስቲ ልየው› ብሎኝ አሳየሁት፡፡ ከመጽሐፉ ጋር ተያይዞ ባነሳቸው ጥያቄዎችና ነቀፌታዎች የተነሳ የሚከተለውን ክርክር ተጨቃጭቀን ተለያየን፡፡
ልጁ ክርክሩን የጀመረውም “አሁን ይህንን መጽሐፍ ብለህ ታነባለህ?” በሚል ነበር፡፡
እኔም ተናድጄ “ለምን አላነበውም መጽሐፍ አይደለም?” ብዬ በጥያቄ መለስኩለት፡፡
“ማለቴ በዚህ መጽሐፍ ጊዜህን ከምታባክን ለምን የተሻለ እውቀት ያላቸውን መጻሕፍት አታነብም?”
“ምን ዓይነት መጻሕፍት ናቸው የተሻለ ዕውቀት ያላቸው?”
“ለምሳሌ የፍልስፍና መጻሕፍትን አታነብም? ሰዎች ለጥቅማቸው ሲሉ እግዚአብሔር ፣ ሰይጣን፣ ኃጢያት፣ ጽድቅ፣ ኩነኔ ምናምን እያሉ የጻፉትን ተረታተረት ከምትለቃቅም?” አለኝ እያጣጣለ፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jun 25, 2014

ምኒልክ እና አርሲ - (ወርቁ ፈረደ)

Geez Bet | Wednesday, June 25, 2014
ኢትዮጵያዊው ቢስማርክ ዳግማዊ ምኒልክ፣ አገር ለማስገበር ካደረጓቸው ዘመቻዎች ውስጥ ትልቅ ምከታ የገጠማቸው አርሲ ላይ ነው፡፡ ምኒልክ በአርሲዎች ክንድ ተከታታይ ሽንፈት ከቀመሱ በኋላ፣ በራስ ወልደ ገብርኤልና በራስ ዳርጌ እልክ አስጨራሽ ዘመቻ አማካኝነት፣ አሸንፈው አርሲን ወደ ግዛታቸው ቀላቀሉት፡: በጦርነቱ ከአስገባሪውና ከገባሪው ወገን አያሌ ወታደሮች አልቀዋል፡፡
ውጊያው የተካሄደው፣ነፍጥ በታጠቁ የንጉሱ ወታደሮችና ከጦርና ጋሻ ፈረስ ውጭ ምንም በሌላቸው የአርሲ ጎበዞች መካከል በመሆኑ፣ ከተከላካዩ ወገን ያለቀው በቁጥር እንደሚልቅ እሙን ነው፡፡ የአርሲ ጦርነት ከተካሄደ ከጥቂት አመታት በኋላ፣ ወደ ኦሮሞ ምድር የደረሰው ደ ሳልቪያክ የተባለ የፈረንሳይ ሀዋርያ ከአርሲዎች በሰበሰበው መረጃ ተመስርቶ እንደጻፈው፣ ራስ ወልደገብርኤል የአርሲዎችን አይበገሬነት ለመስበር ባንድ ቀን ብቻ የአራት መቶ አንጋፋዎችን ክንድ አስቆርጠዋል፡፡ይህ ጻሀፊ፣ ክንዳቸውን ካጡት ትልልቅ ሰዎች ጥቂቶቹን ባይኔ በብረቱ አይቻለሁ ብሏል፡፡
            ይህ የታሪክ ዘገባ በዘመናችን ፖለቲከኞች ሁለት ዓይነት ምላሽ እየተሰጠው ነው፡፡ የመጀመሪያው ምላሽ ክስተቱን ‹‹አይደረግም›› ብሎ መካድ ሲሆን፤ በተቃራኒ ወገን ያለው ደግሞ በማጋነንና በማራገብ ተጠምዷል፡፡ባለፈው ሳምንት ሀብታሙ አያሌው የተባለ ጸሀፊ በዚህች መጽሔት ላይ ሲጽፍ፣ የአርሲን የበደል ታሪክ፣ የቡርቃ ዝምታ ልቦለድ ውጤት እንደሆነ ሊያሳምነን ይፈልጋል፡፡ በኔ አስተያየት ይሄ አይነቱ ድርቅና ማንንም አይጠቅምም፡፡ አርሲ በስጦታ ወይም በስምምነት የተደባለቀ አገር አይደለም፡፡ የተገኘው በብዙ አገሮች እንደተደረገው፣ በጉልበትና በነውጥ ነው፡፡በወቅቱ ሰብአዊ ጥሰቶች በገባሪው ወገን ላይ መድረሳቸውን መካድ አስፈላጊ አይደለም፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

አንዲት ኢትየጵያዊት በጅዳ ቆንስል ግቢ ታንቃ ተገኘች

Geez Bet | Wednesday, June 25, 2014
በሳውዲ አረቢያ ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ግዜያዊ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ እንዲት ኢትዮጵያዊት ታንቃ መገኘቷ የአካቢውን ማህበረሰብ ደረት ሲያስደቃ መዋሉን ቦታው ላይ የነበሩ የአይን እማኞች አረጋግጠዋል። ዛሬ በኢትዮጵያ ሰአት አቋ ጣጠር ከቀኑ 10
ሰአት ቆንስላው ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ታንቃ የተገኘቸው ወጣት በ 20 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ መሆኗን የሚናገሩ እማኞች በኮንተራት ለስራ መጥታ ከአሰሪዎቾ ባለመስማቷ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ግዜያዊ መጠለያ ኮንቴነር ውስጥ ለረዥም ወራት ስትሰቃይ የኖረች ሳትሆን እንደማትቀር ይናገራሉ ; ፡ በኢትዮጵያ ሰዓት አቋጣጠር ዛሬ ከቀኑ 10 አካባቢ እዚህ ቆንስላ ግቢ ውስጥ የታነቀቸውን ወጣት በአይናቸው ለማየት እድል ያገኙ እማኞች ወጣቷ እራሷን አንቃ ለመግደል ስትወራጭ አንገቷ ውስጥ የገባው ገመድ መስል ነገር ጉሮሮዋን ቆርጧ ወዲያው ሳይገድላት እንዳልቀረ ይገልጻሉ።

ይህ ዜና እስከ ተጠናከረበት ግዜ ድረስ የወጣቷ ሬሳ አለመንሳቱን የሚናገሩ ምንጮች በአካባቢው የፓስፖርተ እድሳት እና መስል ተዘማጅ ጉዳዩቹን ለማስፈጸም የቆንስላ ግቢውን አጨናነቀው እምባ ሲራጭ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ከቆንስላው ጽ/ቤት እንዲወጡ መደረጋቸውን የአይን እማኞቹ አክለው ገልጸዋል ። ይህ በዚህ እንዳለ የሬሳ ጉዳይ የሚከታተለው እና የቀድሞ የኮሚኒቲ አመራር አቶ መሃመድ ሸህ ተፈቅዶለት ወደ ግቢው ሲገባ ያዩ ምንጮች ቦታው ላይ የሳውዲ ፖሊሶች እና ዲፕሎማቶች መገኘታቸውን
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jun 23, 2014

በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ወራሪው ማን ነው? ተወራሪዎቹስ?

Geez Bet | Monday, June 23, 2014
በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ታላቅ የሕዝብ ቅልቅል ተካሂዷል። ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል፦ የአህመድ ግራኝ ወረራ፣ የኦሮሞ ወረራ፣ በዘመነ መሣፍንት የነበሩት የእርስ በእርስ ጦርነቶች፣ ፈፃሜ-ዘመነ
መሣፍንትን ያበሠሩት የማዕከላዊ መንግሥትን እንደገና የማዋቀር ጦርነቶች እንዲሁም ሁለቱ የኢጣሊያ ወረራዎች የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚያ ጦርነቶች እና የእርስ በእርስ ግጭቶች ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የሕዝብ ክፍል ሕይዎት እንዳሣጡ አይካድም። ያንንም ተከትሎ ከኑሮ አስገዳጅነት እና በአገዛዝ ኃይሎች የበላይነት የያዘው አካል በሚፈጥረው የፖለቲካ አሠላለፍ መለዋወጥ ምክንያት የአንዱ ጎሣ ወይም ነገድ አባሎች በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመጥፋት ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዚህ ረገድ ከኢትዮጵያ ዋና ዋና ነገዶች እና ጎሣዎች መካከል፦ በምዕራብ ኢትዮጵያ ነዋሪ የነበሩት የጋፋት ነገድ በኦሮሞ ወረራ ሙሉ በሙሉ እንዲጠፉ ሆነዋል ወይም ማንነታቸውን ተገድደው ለውጠው «ኦሮሞዎች» ወይም «ዐማራዎች» ወይም በሌላ ነገድ ስም ይጠራሉ፤ የሜያ ነገድ ተወላጆች ደግሞ በግራኝ አህመድ እና በኋላም ተከትሎ በመጣው በኦሮሞዎች ወረራ ምክንያት ቁጥራቸው በእጅጉ ተመናምኖ ዛሬ በዝዋይ ኃይቅ ውስጥ በሚገኙ ደሴቶች እና አካባቢው ብቻ ተወስነው ይገኛሉ። ጥንት በባሊ (ባሌ) እና ፈጠጋር (አርሲ) ተስፋፍተው ይኖሩ የነበሩት ሐዲያዎች እና ከንባታዎች በኦሮሞዎች ወረራ ተጨፍልቀው «ኦሮሞዎች» ሲባሉ ቀሪ ወገኖቻቸው በደቡብ ምዕራብ ሸዋ በአንድ ጠባብ አካባቢ በተጨናነቀ ሁኔታ እንዲኖሩ ተገድደዋል። ከዚህ በተጨማሪም፦ አርጎባዎች፣
ሙሉውን አንብብ-Read More

መኢአድ የአባሎች ግድያና እስራት መባባሱን ገለፀ

Geez Bet | Monday, June 23, 2014
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ በየቦታው በአባላቶቼ ላይ የሚደርሰው ግድያና እስራት ተባብሶ ቀጥሏል፤ ይህንንም አወግዛለሁ ሲል ለአዲስ አድማስ ገለፀ፡፡ በምስራቅ ጎጃም ዞን እነማይ ወረዳ ደንጎሊማ ቀበሌ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ምሽት ላይ የፓርቲው የቀበሌ ተጠሪ የነበሩት አርሶ አደር ሞሳ አዳነ በታጣቂ ካድሬዎች ተደብድበው ህይወታቸው ማለፉን መኢአድ ገልጿል፡፡
በወረዳው የፓርቲው ምክትል ሰብሳቢና የዞኑ ወጣቶች ጉዳይ ተጠሪ መቶ አለቃ ደምመላሽ ጌትነት ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፣ ሟቹ አርሶ አደር ከዚህ ቀደም በመኢአድ አባልነታቸው የተነሳ ከእድርና ከቤተክርስቲያን እንዲገለሉ በመደረጋቸው፣ መገለሉ እንዲነሳላቸው ለወረዳው መስተዳደር አቤቱታ አቅርበው ነበር፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

ከአሥር ወራት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ያጡ የፍቼ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሠልፍ ሊወጡ ነው

Geez Bet | Monday, June 23, 2014
-ካህናትና የነዋሪዎች ተወካዮች ዋና መሥሪያ ቤቱን ተማፀኑ:-
ላለፉት አሥር ወራት ከኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ኩራዝ ብርሃን ለመመለስ ተገደናል ያሉ በኦሮሚያ ክልል የፍቼ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች፣ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግ ለከተማው አስተዳደር ጥያቄ ማቅረባቸውን አስታወቁ፡፡

ነዋሪዎቹ ሠልፍ እንደሚወጡ የከተማውን አስተዳደር መጠየቃቸውን የገለጹት፣ ነዋሪዎቹን ወክለውና የከተማውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አባቶችን ልብሰ ተክህኖ በመልበስና ሌሎች የሃይማኖት ተወካዮች እንደእምነታቸው ለብሰው፣ ፒያሳ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ተገኝተው ቅሬታቸውን ባሰሙበት ወቅት ነው፡፡
የፍቼ ከተማ ነዋሪዎች ላለፉት አሥር ወራት የኤሌክትሪክ ኃይል አጥተው መክረማቸውን የመሥሪያ ቤቱ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት እማኝ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፣ ከፍቼ እስከ አዲስ አበባ ከተማ ያሉትን ቢሮዎች ቢያዳርሱም፣ አንዱ ወደ ሌላኛው ቢሮ እንዲሄዱ ከመንገር ባለፈ የፈየዱላቸው እንደሌለ አስረድተዋል፡፡ ብሶታቸው እየባሰ በመምጣቱና ከመንግሥት አንድ ቁርጥ ያለ ምላሽ ማግኘት እንዳለባቸው በማመናቸው፣ ሁሉንም የከተማውን ነዋሪዎች በመወከል ከ25 የሚበልጡ ተወካዮች በዋናው መሥሪያ ቤት ተገኝተው ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More