Time in Ethiopia:

Dec 24, 2014

Ethiopian pilots very likely to have landed at Eritrea-held Assab Port: source

Geez Bet | Wednesday, December 24, 2014

WASHINGTON, DC - An Ethiopian pilot and two of his crew members defected to Eritrea flying an Mi-35 combat helicopter, the state television announced on Monday.
The pilots were based in the eastern city of Dire Dawa and they executed their plan during what the state-owned TV called a "routine flight training." The announcement came in after days of massive aerial search across northeastern Ethiopia.

The crew members were Captain Samuel Giday, Lt. Bililign Desalegn, and flight technician Tsegaberhan Giday. It was not known whether the pilot and technician are siblings.
The TV didn't specify where in Eritrea the pilot landed the helicopter, but an Ethiopian Air Force source cited the Port of Assab as the most likely place of landing the aircraft.
ሙሉውን አንብብ-Read More

የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና – ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ከዝዋይ እስር ቤት)

Geez Bet | Wednesday, December 24, 2014
በእስር ላይ ያለው የተደናቂው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሁለተኛውንና ‹የኢትዮጵያ መንግስት ገበና› የተሰኘው ጦማር ከዝዋይ እስር ቤት ወጥቷል፡፡ ተመስገን አብረውት የታሰሩ የፖለቲከኛ እስረኞች በሚታወቅበት የጋዜጠኝነት ችሎታው እየጠየቀና እያውጣጣ መፈጠራቸው የሚያስምሙ ታሪኮችን ለመልቀም እንደቻለ ጽሁፉን ያነበበ ይረዳዋል፡፡
ክፍል 2
ተመስገን ደሳለኝ
በዚህ አውድ ለማቅረብ የተገደድኩበትን ዘግናኝ ታሪክ፣ ወደር በሌለው አስከፊነቱ የተነሳ ለንባብ ባላበቃው በወደድኩ ነበር፡፡ ግና! ይህ መንግስታዊ የጭካኔ ተግባር፣ ዛሬም በምስኪን ዜጎች ላይ እየተፈፀመና ብዙዎችን ሰለባ እያደረገ በመሆኑ ህዝቡ ይህን ሊሸሸግ እየተሞከረ ያለውን መከራ ተረድቶ ሥርዓቱን በአደባባይ ዓመፅ “ሃይ!” ይል ዘንድ ትርክቴን ለማጠናቀር ተገድጄያለሁ፡፡ ለእስር ያበቃኝ የጋዜጠኝነት ሙያዬም ተጨማሪ ዕዳ ጭኖብኛል፡፡


“ጄል-ኦጋዴን”
ጄል ኦጋዴን በሱማሌ ክልል ርዕሰ-መዲና የሚገኝ፤ ለ800 እስረኞች ታቅዶ በ1992 ዓ.ም የተገነባ እስር ቤት ነው፡፡ የግቢውን ዙሪያ ከከበበው አጥር በግምት 15 ሜትር ፈንጠር ብሎ ሌላ ተደራቢ የድንጋይ አጥር ተበጅቶለታል፡፡ እስከ ሚያዝያ 24 1999 ዓ.ም ድረስ እስር ቤቱ በሌሎች የሀገሪቱ
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 23, 2014

የሕወሓት አስተዳደር የአስመራው መንግስት ሄሊኮፕተሩን በሱዳን በኩል እንዲመልስለት መጠየቁ ተሰማ

Geez Bet | Tuesday, December 23, 2014
(ምንሊክ ሳልሳዊ) ስርአቱን ከዱ የተባሉት አብራሪዎች ከድሬዳዋ ተነስተው በጅቡቲ ድንበር አስታከው በአሰብ ዘልቀው ኤርትራ ያሳረፉት ሄሊኮፕተር በሱዳን በኩል እንዲመለስለት ሻእቢያን መጠየቁን የሱዳን ዲፕሎማቶች ጠቆሙ::
ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርገውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በአየር ሃይሉ ውስጥ የሚፈጸመውን ደባ በመቃወም ከድተዋል የተባሉት 2 ፓይለቶች(ካፒቴን ሳሙኤል እና ቢሊሊኝ )እና አንድ ቴክኒሽያን(ጸጋ ብርሃን)ለኤርትራ መንግስት እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ይህንንም የወያኔው ቴሌቭዥን ጣቢያ እማኝነቱን ሰቷል::
አብራሪዎቹ ይዘውት የሄዱትን ሄሊኮፕተር እንዲመለስለት ወያኔ የሱዳን ዲፕሎማቶችን የላከ ሲሆን ሻእቢያ የማይመልስ ከሆነ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ከባድ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አንድ ለስርአቱ ቅርብ የሆነ ድህረገጽ ጽፏል::
በሃገር ውስጥ እና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ፖለቲካ ድል ሲቆጥሩት አንዳንዶቹ ወያኔ የሻእቢያን አየር ሃይል በሰው ሃይል እየገነባ ሊሆን ይችላል ከጀርባ ሌላ ደባዎች በወያኔ እና ሻእቢያ ሊሰራ ይችላል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አልጠፉም::የወያኔ መክላከያ ሰራዊት አጸፋዊ እርምጃ ይወስዳል የሚል ስጋት ቢያይልም;ሃገር ወዳዶች ግን ምንም እርምጃ አይወስድም የፍርሃት ዛቻ ነው ሲሉ ተደምጠዋል::
ሙሉውን አንብብ-Read More

Ethiopia: Pilot Hijacked Our Military Helicopter to Eritrea

Geez Bet | Tuesday, December 23, 2014
The Ethiopian Defense Ministry charges that a pilot hijacked to Eritrea an attack helicopter which went missing a few days ago.
In a statement issued late Monday the ministry said the pilot of the Ethiopian attack helicopter forced his co-pilot and technician to land in Eritrean territory.
The helicopter was conducting a routine training flight when it disappeared on Friday morning, prompting a massive military search across northern Ethiopia.
It's unusual for Ethiopian army personnel to flee to Eritrea though Eritrean troops often across the border into Ethiopia, citing harsh conditions and forced conscription into the military.
Relations between Eritrea and Ethiopia have been consistently strained since Eritrea gained its independence from the Addis Ababa government in 1993 following a 30-year guerrilla war.

Source: ABC News
ሙሉውን አንብብ-Read More

Oct 9, 2014

‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ብሎ ለጠየቀ!

ZETOBIA | Thursday, October 09, 2014

(በካሣሁን ዓለሙ)

‹ፍልስፍናን እማራለሁ› ብዬ ት/ቤት ብገባ፣ መምህሩ ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ብሎ መልሶ እኔኑ ጠየቀኝ፤ ‹ካወቅኳትም ለም
ንስ ልማራት ሒሳብ ከፈልኩ?› አልኩኝ፤ ምን ላድርግ? ቢቸግረኝ ያው ‹የፍልስፍና አስተማሪዎች ናቸው› ከሚባሉት ፋይል የሰማሁትን ስምምነታቸውን ይዤ፡- ፍልስፍና እኮ እንዲህ ነው ማለት ጀመርኩ!
በመሠረቱ ጭንቁ መልሱ ላይ ነው እንጂ የፍልስፍና አዋቂና ምጡቅ የተባለ ሁሉ ይችን ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› የምትል ጥያቄ ሳያነሳት አይቀርም፤ መምህሬም ‹ጥያቄዋ ትንሽ ገብታው ነው› መሰል የጠየቀኝ፤ እንደኔ ያላብላሉት ሳይሆኑ መልሷን ሲጭሩ የኖሩት ሊቃውንት ግን ግምታዊ መልሳቸውን ሰጥተዋል፤ እኔም በመጠኑ ሰምቻለሁ (ከፈለጋችሁ ጆሮ ጠገብ በሉኝ)፡፡ በአጠቃላይ ግን በሊቃውንቷ ‹ፍልስፍና ጥበብን ማፍቀር ናት› የሚል ስምምነት ላይ ተደርሶባታል ብሏል መምህሬ ራሱ፡፡ እንደዚህ ከሆነማ ማጠንጠኛዎቿ እነዚህ ‹ጥበብ› እና ‹ፍቀር› የሚሉ ቃላት (ጽንሣተ-ሐሣብ) ናቸው ማለት ብዬ ያዝኩ፡፡ እነዚህ ሁለት ቃላት ደግሞ ዓለምን በመሠረትነትና በዓምድነት (ምሠሦ ሆነው) ያቆሙ ኃይላት ናቸው፡፡ የፍልስፍናም ድንቅነት የተመሠረተው በእነሱ የውህድነት ጥንጣኔ ላይ ሊሆን ነው፡፡ መምህሬም ጥያቄዎቹን አከታተለ ‹እንዴት ተዋሃዱ? የውህደታቸው ጥብዓትስ እስከምን ድረስ ነው? በምን ያህል አስተውሎትስ ልንረዳቸው ቻልን? የእሴትና የኪን (የውበትን) ተውህቦስ ማን አደላቸው? ነው በራሳቸው በሌጣነት ነው አንክሮ ውስጥ የከተቱን?› የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እያነሳ አስጨነቀን! እንደተረዳሁት ከሆነ በእነሱ የተነሣ ስንቱ ሊቅ ቀውሷል፣ ስንቱም አሰላሳይ ከዘመድ ከወዳጅ ተለይቶ መንኖላቸዋል መሰላችሁ፤ ጥበብን ማፍቀር አያድርስባችሁ እቴ! (እንቢ ካላችሁም የጥበብ ስቃይን ይጣልባችሁ ብሎ መርገም ይቻላል!)
ያሳቢዎቹን ምጥቀት የፈተነውስ ጥበባዊ ፍቅሯ አይደል! ስለዚህ መምህሬም ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ሲል የፍቅርንና የጥበብን ምንነት ያውቃል ማለት ነው፤ ስለዚህ እኔ ያልገባኝ ‹ፍቅር ራሱ ምንድን ነው? ጥበብስ ለምን ልትፈቀር ቻለች?› አልኩት! እሱም በገፅታው ‹ደደብ!› እያለ በቃላት ተረከልኝ! ትንሽ አሰላስሎም ገለጻውን ‹ፍቅርን› ሊተረጉም በመሞከር ጀመረ!
ሙሉውን አንብብ-Read More

Aug 27, 2014

የፕሮፌሰር ጌታቸው ነገር! (ወርቁ ፈረደ)

Geez Bet | Wednesday, August 27, 2014
ብሄርተኝነትን ታጥቀው አገራችንን ወደ አደገኛ ጠርዝ ከሚገፏት ምሁራን መካከል፣ የተወሰኑት ላይ የአቅሜን ያህል ሂስ ለመሰንዘር ሞክሬያለሁ፡፡ አሁን ደግሞ የፕሮፌሰር ጌታቸውን አንዳንድ የተዛቡ ሀሳቦች ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡
ፕሮፌሰር ጌታቸው አንቱ የሚባሉ ምሁርና አንተ የሚባሉ ፖለቲከኛ ናቸው፡፡ ጥናቶቻቸውን አንብቦ በእውቀታቸው ስፋት እና በጽሁፍ ችሎታቸው የማይደነቅ ሰው ማግኘት ይከብዳል፡፡ ያም ሆኖ ጌቾ በመጣጥፎቻቸው፣ በግለ ታሪካቸው፣ እንዲሁም የአባ ባህርይ ድርሰቶችን በሰበሰቡበትና ባሰናዱበት ጥራዛቸው የሚያንጸባርቋቸው አንዳንድ የተዛቡና አደገኛ ሐሳቦች አብረው የሚያኗኑሩ አይደሉም:፡
ለምሳሌ በቅርቡ፣ በአንዳንድ የኦሮሞ ብሄርተኞች በኩል ለሚሰነዘሩ ዘለፋዎች ምላሽ እንዲሆን የጻፉትን “ዕርቅና ሰላም፣ የሕይወት ቅመም” የተባለ መጣጥፋቸውን ያነበበ ሰው፤ አንጋፋ ምሁራኖቻችን ከዕርቅና ከሰላም ጋራ እንዴት አድርገው እንዳቆራረጡን መረዳት አያቅተውም፡፡
ጌቾ፣ ለአገሪቱ ቅርስ ውድመት የእስልምና እምነትና የኦሮምኛ ተናጋሪ ጎሳዎችን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡ እርግጥ ነው፣ የግራኝ አህመድ ጦር ወደ መሀል አገር በዘመተ ጊዜ እንዲሁም የኦሮሞ ገዳ ጦር አንዳንድ የአገሪቱን ክፍሎች በጦር ባስገበረ ጊዜ አያሌ ሰብአዊ፣ ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብቶች ላይ ውድመት መድረሱ የተረጋገጠ ነው፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

“በበዓሉ ግርማ ጉዳይ ላይ ከሕሊና ዕዳ ነጻ ነኝ” ደራሲና ሐያሲ አስፋው ዳምጤ

Geez Bet | Wednesday, August 27, 2014
asfaw_damte
ደራሲና ሐያሲ አስፋው ዳምጤ ናደው፣ የተወለዱት መጋቢት 1ዐ ቀን 1927 ዓ.ም. አዲስ አበባ ጊዮርጊስ አካባቢ፣ መርሐ ጥበብ
ማተሚያ ቤት ግቢ ከሚባለው ቦታ ነው፡፡
አቶ አስፋው የቤተ ክህነት ትምህርት ለጥቂት ጊዜ ከተማሩ በኋላ፣ በዘመናዊ ትምህርት፣ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃን፣ በኮከበ
ፅባሕ ቀ.ኃ.ሥ. አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በመጀመሪያ ዲግሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ
በእንግሊዙ ኪምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ተምረው ተመርቀዋል፡፡
ወደሥራ ዓለም ከተቀላቀሉ በኋላ፣አብዛኛውን የሥራ ጊዜያቸው በገንዘብ ሚኒስቴር በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ያገለገሉ ሲሆን፣
ከገንዘብ ሚኒስቴር እንደለቀቁ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ድርጅትና በኩራዝ አሳታሚ ሠርተዋል፡፡
አቶ አስፋው ከኢትዮጵያ ውጭ ካሳለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ፣ በእንግሊዝ ለትምህርት ሶስት ዓመት፣ ቀሪውን አራት ዓመት
ደግሞ በአሜሪካ በሥራ ነበር::

በድርሰቱ ዓለምም፣ “አንድ ለአምስት” የተሰኘ ረጅም ልቦለድ ያበረከቱ ሲሆን፣ በደራሲያን ማኀበር ካሳተመው በ“የዘመነ
ቀለማት” መፍሐፍ ላይ በአጫጭር ግጥሞቻቸው፣ በ‹‹እነሆ››መድብል ደግሞ በአጫጭር ታሪኮች ተሳትፈዋል፡፡ከዚህም
በተጨማሪ ከ1970 እስከ 90ዎቹ ዓመታት ድረስ ስለ አማርኛ ጥበበ ቃላት አንዳንድ ነጥቦችን ከስር ጀምረው መጣጥፎችን
ሙሉውን አንብብ-Read More

Aug 8, 2014

አገሬ ታማለች!

ZETOBIA | Friday, August 08, 2014

አገሬ ታማለች!


(በካሣሁን ዓለሙ)
እማማ ታማለች፣
አገሬ ታማለች፣
ሆስፒታል ተኝታ
እ!እ!…ህእ!ም!…ህም!!! ትለኛለች፤
ከህቅታዋም ውስጥ ጣሯ ይሰማኛል፣
ህመሟን ስቃዩዋን፣
ዝም ብዬ እየሰማሁ፣
እማዬ! እላታለሁ፤
ህመሟ ያመኛል፣
ጧሯ ይነዝረኛል፣
አዎ! እማማ ታማለች፣
ይኸው በሆስፒታል
እ!!…ህ!!!.. እህ!!!… ትለኛለች፤
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jul 14, 2014

የአንዳርጋቸው ጽጌ የእንግሊዝ ፓስፖርት

Geez Bet | Monday, July 14, 2014
ማክሰኞ ምሽት ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ኢቲቪ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አስመልክቶ ያቀረበው ዜናን ብዙዎች በተቀላቀለ ስሜት ነበር የተከታተሉት፡፡
ዜናው የአቶ አንዳርጋቸውን ንግግር ለአፍታ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱ ግን ግራ ያጋባቸው በርካቶች ናቸው፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ‹‹እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ፡፡ እውነቴን ነው የምልህ እኔ እንደ ምርቃት ነው የተቀበልኩት፡፡ አሁን የሚያስቸኩለኝ ነገር የለም፡፡ ጥሩ ዕረፍት ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ ምክንያቱም በጣም በጣም ደክሞኛል … ሰልችቶኛል፡፡ እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ጥላቻ በውስጤ የለም፡፡ ምንም ዓይነት ብስጭት የለኝም፡፡ ምንም ዓይነት መጥፎ ስሜት አይሰማኝም፡፡ በቃ … የመጨረሻ እርጋታና ዕረፍት ውስጥ ነው ያለሁት፤›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከአንዴም ሁለቴ በፍርድ ቤት በሽብርተኝነት ከሶ የሞት ፍርድ ባስፈረደ መንግሥት ቁጥጥር ሥር የዋለ ሰው በጤናው ደስተኛነቱን አይናገርም የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች፣ የንግግሩን አንድምታ በተመለከተ የተራራቀ መላምታቸውን ማቅረባቸውን ቀጥለዋል፡፡ ለአንዳንዶች የአቶ አንዳርጋቸው ንግግር ባልተጠበቀ መንገድ በጠላቶቹ እጅ የወደቀ ሰው ያለበትን ሁኔታ ባለመቀበል የሰጡት ነው፡፡ ለሌሎች ደግሞ በአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ ሁኔታ ላይ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እያሰማ ላለው ሥጋት ምላሽ ለመስጠት መንግሥት አስገድዷቸው የሰጡት ቃል ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልገሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረ ኃይል አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሰንዓ በኩል ወደ ኤርትራ ሊገቡ ሲል ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው፣ በዚያው ዕለት ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታ
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jul 8, 2014

አይ አበሻ! አበሻና ቀጥታ መስመር [ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ-ማርያም]

Geez Bet | Tuesday, July 08, 2014
አበሻና ቀጥታ መስመር አይተዋወቁም፤ ቀጥታ መስመር መጀመሪያ አለው፣ መጨረሻም አለው፤ አበሻ እንዲህ ተጀምሮ የሚያልቅ ነገር አይወድም፤ እልቅ ሲል ጭር ይልበታል፤ አበሻ የባህርዩ የሆነውና የሚስማማው ክብ መስመር ነው፣ ክብ መስመር መጀመሪያ የለው፣ ማለቂያ የለው፣ ሲዞሩ መዋል ነው፤ አበሻ ነገሩ ሁሉ ክብ ነው፤ ቤቱ ክብ ነው፣ እንጀራው ክብ ነው፣ ዳቦው ክብ ነው፣ ድስቱ ክብ ነው፣ ጋኑም ክብ ነው፤ ክብ ያልሆነ
ነገር አበሻ ምን አለው?
አበሻ ነገሩ ሁሉ ክብ ነው፣ አዙሪት ነው፣ ታሪኩም አዙሪት ነው፣ ሄደ የተባለው ሁሉ ተመልሶ ይመጣል። አበሻ ማለት አዙሪት ነው፣ አዙሪት ማለትም አበሻ ነው። የእንግሊዝ ወይም የሩስያ ወታደሮችን ሰልፍ ስታዩ ቀጥታ መስመር ምን እንደሆነ ተገነዘባላችሁ። የአበሻ ወታደሮችስ? ተለያይቶ የተገጣጠመ ክብ መስመር?
አበሻ በመስመር መሄድም ሆነ መቆም አይሆንለትም። አበሻ ቀጥታ መሰመር ሲያጋጥመው የሚታየው ተለምጦ ነው፣ ክብ ሆኖ ነው፣ መጀመሪያ የሌለው፤ መጨረሻም የሌለው በፈለገበት በኩል ሊገባበትና በፈለገበት በኩል ሊወጣበት የሚያስችለው ክብ ሲሆን ነው፤ ሰዎች ተራ ይዘው በመስመር እንዲጠብቁ በሚደረግበት ግዜ አበሻ ጭንቀቱ ነው፤ እንዴት ብሎ ጀርባውን ለማያውቀው ሰጥቶ ከፊቱ ደግሞ አንድ የማያውቀው ሰው ተደንቅሮ በሰላም መቆም ይችላል? አንዱ ደፋር ከኋላው መጥቶ ቀድሞት ቢሄድ ግድ የለውም፤ ለነገሩ ራሱም ቢሆን ፈርቶ ነው እንጂ ያደርገው ነበር! የድሮዎቹን ሰዎች ጭንቀታቸውን ለመቀነስ አንተ ቅደም አንተ ቅደም እየተባባሉ የተራውን ቀጥታ መስመር ይቆለምሙት ነበር፤ የዛሬው የሰለጠነው ትውልድ አንተ ቅደም ብሎ ነገር አያውቅም፣ ሁሉም በየፊናው ለመቅደም ሲሞክር መተራመስ ነው፤ መተራመስ ቀጥታ መስመርን ድራሹን ማጥፋት ነው።
ሙሉውን አንብብ-Read More

ኢትዮጵያውያን ባሎች ሚስቶቻቸውን በመደብደብ ከአፍሪካ 3ኛ ናቸው

Geez Bet | Tuesday, July 08, 2014

87 በመቶ የማሊ ሴቶች ድብደባ ተገቢ ነው ይላሉ:: 
የጊኒና የኢትዮጵያ ሴቶችም ድብደባ ተገቢ ነው ብለው ያስባሉ:: 
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ተቋማት በቤት ውስጥ ጥቃት ዙሪያ ያወጧቸውን ሪፖርቶች መነሻ በማድረግ በቅርቡ በ37 የአፍሪካ አገራት ላይ የተሰራ አንድ ጥናት፣ ኢትዮጵያውያን ባሎች ሚስቶቻቸውን አዘውትረው በመደብድብ 3ኛ መሆናቸውን አረጋገጠ።
‘አፍሪካ ሄልዝ፣ ሂዩማን ኤንድ ሶሻል ዲቨሎፕመንት ሰርቪስ’ የተባለው አህጉራዊ ድርጅትና በሴቶች ጥቃት ዙሪያ የሚሰሩ ሌሎች ተቋማት በጋራ የሰሩት ጥናት እንደሚለው፣ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ባሎች የትዳር አጋሮቻቸውን መደብደብ አግባብ ነው ብለው የሚያስቡና በተለያዩ ምክንያቶች ሚስቶቻቸውን የሚደበድቡ ናቸው፡፡ 
ጥናቱ ከተሰራባቸው የአፍሪካ አገራት የበለጠ ተደባዳቢ ባሎች ያሉባት አገር ናት ተብላ በቀዳሚነት የተቀመጠችው ኡጋንዳን ስትሆን፣ ሴራሊዮን ሁለተኛ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ ሶስተኛ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Jul 7, 2014

ድኻው ምን አረገ

Geez Bet | Monday, July 07, 2014
ዳንኤል ክብረት: -
ሰሞኑን ከአንድ ሰው ‹የማጭበርበር› ነገር ጋር በተያያዝ ከዚህም ከዚያም አስተያየት ይሰጣል፡፡ አብዛኞቹ የመገናኛ ብዙኃንም ትኩረታቸውን በሰውዬው ላይ አድርገው እንዴት እንዲህ ሊያደርግ ቻለ? ለምን እንዲህ አደረገ? ምን ነክቶት ነው? እያሉ ጉዳዩን ከማኅበረሰብ ሳይንስ፣ ከሥነ ልቡና፣ ከእምነትና ከባሕል አንጻር እየተነተኑ ይገኛሉ፡፡
እኔ ግን ይህን ጉዳይ ስከታተል ትዝ የሚለኝ አንድ የሀገራችን ተረት ነው፡፡ ሰውዬው መንገድ ላይ ሲሄድ በሩ ወለል ብሎ የተከፈተ ቤት ያገኛል፡፡ ለጥቂት ቆም ብሎ ሁኔታውን ሲያይ ማንም በአካባቢው ዝር የሚል አልነበረም፡፡ ነገሩ የተከፈተ በር ብቻ ሳይሆን ‹የተከፈተ ዕድልም› የሆነለት ሰውዬ የተከፈተው ቤት ውስጥ ዘው ብሎ ይገባል፡፡ማንም አልነበረም፡፡ ወዲያና ወዲህ እየተንጎራደደ ቤቱን ቃኘና ዓይኑ ያረፈበትን ዕቃ ይዞ ላጥ አለ፡፡ መንገድ ላይ ያዩት ሰዎች የሚያውቁትን ዕቃ አንድ ሰው ይዞ ሲሸመጥጥ በማየታቸው ይጠራጠሩና ያስቆሙታል፡፡ ፖሊስም በነገሩ ይገባበታል፡፡ ሰውም ከዚህም ከዚያም ይወርድበታል፡፡
      ግርግሩ በዚህ መልክ እየቀጠለ ዕቃቸው የተሰረቀባቸው ሰዎች ኡኡ እያሉ ይደርሳሉ፡፡ ሲደርሱም የቤት ዕቃቸው በአንድ በማያውቁት ሰው ትከሻ ላይ ያገኛሉ፡፡ ግርግሩን ሰንጥቀው ይገቡና ‹‹ሞላጫ ሌባ›› እያሉ ሌባውን በጥፊ ሲመቱት ሌባው ተናድዶ ዕቃውን ያወርድና ጥፊውን በጥፊ ይመልሳል፡፡ ፖሊስ በድርጊቱ ተገርሞ ከዚያ ሁሉ ሰው ይልቅ ለባለቤቶቹ ጥፊ ለምን መልስ እንደሰጠ ሲጠይቀው ‹‹ቤታቸውን ከፍተው እየሄዱ ሰው ሌባ ያደርጋሉ›› አለ ይባላል፡፡
የሰሞኑ ሁኔታም ይህን ነገር እንድናየው የሚያደርግ ነው፡፡ ለመጭበርበርና ለመታለል የሚችል አሠራር፣ አካሄድና አፈጻጸም የዘረጋነው እኛው ነን፡፡ ነገሮችን በመረጃና በማስረጃ ላይ ተመርኩዘን ከመወሰን ይልቅ በሚወራ ወሬ፣ በሚገነባ ገጽታና ከሚዲያ በምንሰማው ነገር ላይ ብቻ የመመራትን አሠራር ያሰፈንነው እኛው ነን፡፡ ዛሬ ቀን ጥሎት የተጋለጠው ሰው ላይ በወደቀ ዛፍ ላይ የሚበዛውን ምሣር ሁሉ እናዘንብበታለን እንጂ ሌሎች ወደፊት እንዳይከሰቱ የሚያደርግ አደረጃጀት፣ አሠራርና አስተሳሰብ ግን አልዘረጋንም፡፡  
ሙሉውን አንብብ-Read More